
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች ላፕቶፕ እና ታብሌት ድጋፍ አደረገ ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ካበረከታቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች 85 ታብሌቶችና 10 ላፕቶፖች በዛሬው ዕለት ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች አስረክቧል ።
አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ባደረጉ የመክፈቻ ንግግር ለድንገተኛ ወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት በመገንባት በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞች በማህበረሰቡ ላይ የከፋ የጤና ጉዳት አንዳያደርሱ በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ የጤና አገ/ት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመረጃ ስርዓቱን ወቅቱን በሚመጥንና ዘመኑን በዋጀ ሂደት ለመምራት እና በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በአፋጣኝ መቆጣጠር የሚያስችል የመረጃ ስርዓቱን ለማሳለጥ በዛሬው ዕለት በስጦታ የሚበረከቱ ታብሌቶችኛ ላፕቶፖች አጋዥ መሆናቸውን በማመላከት ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።
አቶ መሀመድአሚን በደዊ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የጤና ሀብት ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ባስተላለፉት መልዕክት የመረጃ ጥራት ለይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አጋዥ የሆኑ ቁሳቁሶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።



