
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ የሆስፒታሉን ‘የታካሚ ደህንነት አጠባበቅ ሂደት እና የተገኘውን ለውጥ’ በአለም የጤና ድርጅት 41ኛው አለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ ዘርፍ የጥራት ዓለም አቀፍ ማኅበር (ISQua) ጉባኤ ላይ አቅርበዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ በአለም አቀፉ ፕሮግራም ተገኝተው የተቋሙን ‘የታካሚ ደህንነት አጠባበቅ ሂደት እና የተገኘውን ለውጥ’ በማካፈላቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው ለዚህም የሆስፒታሉን ማህበረሰብ፣ የስራ አመራር ቦርድን፣ ስልጤ ልማት ማህበርን፣ የክልሉን ጤና ቢሮ ፣ ጤና ሚኒስቴርንና አጋር አካላትን የፕሮግራሙን መጠናቀቅ ተከትሎ ባጋሩት ጽሁፍ አመስግነዋል።
በሆስፒታሉ የቴሌግራም ግሩኘ ላይ ያጋሩትን መልዕክት ተከትሎ የማኔጅመንት አካላት፣ እስፔሻሊስት ሀኪሞች እንዲሁም አጠቃላይ ባለሙያዎች ሀሳብ አስተያየታቸውን በመስጠት ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛል።
የተቋሙ ተግባር በአለም አቀፍ መድረክ መቅረቡ ለተቋሙ፣ ለክልሉ ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በህክምና ተቋም የታካሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እና ሌሎች የጤና ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያግዛል ብለዋል።



