Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ማህበረሰቡ ፣ባለሀብትና መንግስት በማስተባበር ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለጤና ተቋማት ግብዐት ማሟላት እንደተቻለም ተገለጸ።

“በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ ” በሚል መሪ ቃል የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 ማጠቃለያ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የማህበረሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋነኛው አማራጭ የጤና መድህን አጋግሎት መሆኑ ተገልጿል!!

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ፣የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ከድጃ ተማም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ ፣የዞኑ ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አየለ ፈቀደ ጨምሮ የዞኑ የምክር ቤት አመራሮች እና የሁሉም መምሪያ ሀላፊዎች ፣የወረዳና የከተማ አስተዳዳሪዎች ፣ ፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *