
የማዕ/ ኢት/ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የጥናት እና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የመረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል በክልሉ ጤና ቢሮ የህብ/ ጤና ኢን/ት እንዲሁም ከዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ለተወጣጡ ባሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው ።
በጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጥናት እና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ስናፍቅሽ አየለ እንደተናገሩት የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ደህንነቱ የተጠበቀና በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ዉሳኔን ተጠቅሞ አዲስ ግኝት ለማዘጋጀት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ ስለመሆኑ አስረድተዋል ።
ከተለያዩ አካላት የተበታተኑ መረጃዎችን ሰብስቦ በአግባቡ ማደራጀት ይገባል ያሉት ዳይሬክተሯ ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ብቻ በመለየት ለዉሳኔ መጠቀም ይገባል ብለዋል
የጥናት እና ምርምር ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ አዲስ ነገር መፍጠር ይገባል ያሉት ደይሬክተሯ ሰልጣኞች በስልጠና የሚያገኙትን እዉቀት እና ክህሎት በተግባር ቀይረዉ የምርምር ስራዎችን ዉጤታማ ለማድረግ ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል
አቶ ሳሙኤል ሀይሉ የህብ/ጤ/ኢን/የመረ/አሰ/ትንተና ማዕከል የዳታ ማናጀር የስልጠናዉን ዓላማ ሲያብራሩ የተበጣጠሰን መረጃ በመሰብሰብ ማደራጀትና ለዉሳኔ ሰጪ አካላት በመስጠት መጠቀም የሚያስችል ስልጠና ስለመሆኑ ጠቁመዋል ።
ከተለያዩ ጤና ተቋማት ጋር በጋር የተሻለ አዲስ ነገር ለመፍጠር ይህ ስልጠና ወሳኝ ስለመሆኑ የጠቆሙት አቶ ሳሙኤል በየደረጃ ያሉ አካላት ለዉሳኔ ሰጪ አካላት የሚጠቅም መረጃን በማደራጀት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ለማዘጋጀት ቁርጠኛ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።
የመረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለ3 ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል።
በሸምሲያ አደም