
የፖሊዮ በሽታ በአገራችን ለብዙ ህጻናት ህመም፣ የአካል ጉዳትና ሞት ምክንያት ከሆኑት በሽታዎች መካከል አንዱ ነዉ። የፖሊዮን በሽታ መከላከል የሚቻለው ህጻናትን በመደበኛና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን ክትባት ስናስከትብ ነው!!
በመሆኑም የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከየካቲት 14-17/2017 ዓ.ም ድረስ በቤት ለቤት ጉብኝት ይሰጣል፡፡ስለሆነም ህፃናት ከዚህ ቀደም የፖሊዮ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም በዘመቻው እንዲከተቡ በማድረግ የወላጅነት/የአሳዳጊነት ሃላፊነትዎን ይወጡ!!!!
