
ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን በመቆጣጠር ያደረገችው ስኬታማ ጥረት በጠንካራ አመራር፣ ፈጣን ምላሽ እና በተቀናጀ እርምጃ ትልቅ የህብረተሰብ ጤና ስኬትን ማስመዝገቧን የኤፌዴሪ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ ገልፀው፤ ስኬቱ የጤና ፖሊሲ፣ የጤና ባለሙያዎች፣ እና ባለድርሻ አካላት የጋራ የመተባበር እና የመደመር ውጤት ነው ብለዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሃገራችን የጤና ታሪክ ትልቅ የስኬት አሻራ የጣለ ተሞክሮ መሆኑን ገልፀው፤ ማህበረሰቡን በማስተባበር ፈጣን ምላሽ በመስጠት ቫይረሱ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
ለተከታታይ 42 ቀናት አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ባለመኖሩ የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ከቫይረሱ ነፃ መሆናችንን አረጋግጠናል ያሉት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ስጋቶችን ለመቆጣጠር የሚያስፈልገውን የቴክኒክ አቅም እና የሰለጠነ የሰው ኃይል እንዳላት ያረጋግጣል ብለዋል። በቫይረሱ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።
መከላከል እና አክሞ ማዳንን ማዕከል ያደረገው የጤና ፖሊስ እንዲሁም ትጉህ እና ብቁ ከሆኑ የጤና ባለሙያዎቻችን ጋር በመሆን ቫይረሱን ድል ማድረገ ችለናል ያሉት የጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጃ ዱጉማ፤ ተባቡረን ከቆምን ማለፍ የማንችለው መሰናክል የለም ብለዋል።
የምክር ቤት አባላት፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቫይረሱን ለመከላከል አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት አውቅና ተሰጥቷል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB



