በክልሉ የእናቶች ጤናን ለማሻሻል ውጤታማ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “ፈጠራና ዘላቂ ፋይናንስ ለጤናማ እናትነት” በሚል መሪ ቃል የጤናማ እናትነት ወር በቡታጅራ ጠቅላላ ሆስፒታል እየተከበረ ይገኛል ። የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የእለቱን ፕሮግራም ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የጤናማ እናትነት ወርን ለእናቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በላቀ ደረጃ ተደራሽ በማድረግ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ የሚሰራበት መሆኑን ተናግረዋል ።…
Read more
