Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Category: News

CERPHI

በጤናው ዘርፍ መሻሻል እንዲመጣ የጥናትና ምርም ስራዎች ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 ዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2018 ቀጣይ አቅጣጫዎች መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሂዷል። ሐምሌ 8/2017 ሀላባ ቲቪ —————————- በመድረኩ ላይ ለዕለቱ የተዘጋጀ ሰነድና የአፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ምላሽና ማብራሪያውን የሰጡት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙዔል ዳርጌ በክልሉ የወባና ኮሌራ ወረርሽኝን የመቆጣጠር ልምድ እየዳበረ መምጣቱን አስታውሰው…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመታዊ ጉባኤውን በወራቤ ከተማ እያካሄደ ነው።

(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 8/2017)፤ ኢንስቲትዩቱ በመድረኩ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የበጀት አመቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንዳሉት በተጠናቀቀው በጀት አመት አምስት የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት መሠራቱን አንስተዋል። ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋንን ማፍጠን፣ የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታን ማሻሻል፣ ህብረተሰቡን ከድንገተኛ አደጋ መጠበቅ፣ የጤና…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በህብረተሰብ ተሳትፎ ግንባታው የተጠናቀቀውን ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ መርቆ ስራ አስጀመረ::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በህብረተሰብ ተሳትፎና በክልሉ መንግስት ገንዘብ ወጪ የተገነባውን የንቡር ሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ ስራ አስጀመረ። ለሁሉ አቀፍ ጤና ኬላ ግንባታው የአካባቢው ህዝብና የክልሉ መንግስት ከ13ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጋቸው ተገልጿል። የጤና ተቋሙን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የብልጽግና መንግስት…
Read more

ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር ይገባል፡-ጤና ሚኒስቴር::

ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር ይገባል፡-ጤና ሚኒስቴር ********** በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ድጋፎች በመቀነሳቸው፣ ለጤናው ዘርፍ የሚውል ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በራስ አቅም ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ የሚመክር ዓውደጥናት ተካሂዷል። በመድረኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ድጋፎች መቀነሳቸውን ያነሱት የጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ፤ ለዚህ…
Read more

የቴክኖሎጂ አሰራር ስርዓትን በመከተል ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ተጋላጭነት ስጋትን ለማስቀረት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ ፡፡

ሶስተኛው ዙር የክልሉ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የ2018 በጀት ዓመት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የተጋላጭነት ስጋት ልየታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሀዲያ ዞን ሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች አስተዳደር አስተባባሪዎች ስልጠና በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። የክልሉ ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮ ባስተላለፉት መልዕክት በቴክኖሎጂ የታገዘ የህብረተሰብ…
Read more

በተቀናጀ ጤና ዘመቻ በተሰሩ ሥራዎች የሚታይ ለውጥ መመዝገቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በበጀት ዓመቱ በተቀናጀ ዘመቻ የተከናወኑ ተግባሮች ግምገማና እውቅና የመስጠት መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ እንዳሉት፦ በተቀናጀ ጤና ዘመቻ በተሰሩ ሥራዎች የሚታይ ለውጥ ተመዝግቧል። አቶ አሸናፊ፦ በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተከተቡ ህጻናትን በመለየት በቂ የክትባት አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል። በዚህ ሂደት 2…
Read more

በጤናው ዘርፍ ጥራትና ደህንነት በማረጋገጥ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

(ሆሳዕና፣ሰኔ 27/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመታዊ ስራ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሔደ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ እንደገለጹት የጤና ቁጥጥር ስራ ዋነኛ አላማ ህብረተሰቡ በጤናው መስክ የሚያገኛቸው…
Read more

ለሶስት ተከታታይ ቀናት የህብረተሰብ ጤና መረጃ አያያዝ እና ትንተና ላይ ያተኮረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በቡታጅራ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የStat እና R ሶፍትዌር ስልጠና መጠናቀቁን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቋል በስልጠናው ላይ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምርምር ተቋም ባለሙያዎች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጤና ቢሮ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሉ ዩንቨርስቲዎች፣ ኮሌጅዎች ፣ ከዞን እና ልዩ ወረዳ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ከስልጠና መጨረሻ ላይ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማነት መረባረብ እንደሚገባ ገለጸ።

(ሆሳዕና ፡ሰኔ 26/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቡታጅራ ከተማ ያዘጋጀው የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ የንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል። የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማነት የሚያግዙ ሁለት ሰነዶች በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ቀርበዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ሃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ መድረኩን ሲያጠቃልሉ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማነት…
Read more

የእናቶችና ህጻናት ሞትና የሞት መንስኤዎችን አስመልከክቶ የናሙና ምዝገባ ሥርዓት የማስጀመሪያ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ::

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር የእናቶችና ህጻናት ሞት እና የሞት መንስኤዎች እንዲሁም አጠቃላይ የበሽታ ሰርጭት የመለየት እና ያሉትን የክትትል ስርዓቶችን ለማጠናከር የናሙና ምዝገባ ስርዓትን (Sample Registration System/SRS/) ለመዘርጋት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን የማስጀመሪያ የዉይይት መድረክም ሰኔ 24/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ…
Read more