Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Blog

CERPHI

የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠርያ ማዕከል የመድሃኒት እና የህክምና መሣሪያዎች አቅርቦት ለአፍሪካ ሃገራት ለመጀመር የሚረዳ አህጉራዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ::

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ጋር በመተባበር በአፍሪካ የተቀናጀ የመድሃኒት እና የህክምና መሣሪያዎች ግዢ እና አቅርቦት ሜካኒዝም ጅምር ላይ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ውይይት አካሂደዋል፡፡ ሜካኒዝሙ አፍሪካ ሲዲሲ በጋራ በሚሰበሰብ ፈንድ የመድኃኒት ምርቶችን እና ክትባቶችን በመግዛት ለአባል ሀገራት ማሰራጨት እና የሃገር ውስጥ ምርትን ለማበረታታት የሚያስችለው ነው። በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር…
Read more

ማህበረሰቡ ፣ባለሀብትና መንግስት በማስተባበር ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለጤና ተቋማት ግብዐት ማሟላት እንደተቻለም ተገለጸ።

“በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ ” በሚል መሪ ቃል የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 ማጠቃለያ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የማህበረሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋነኛው አማራጭ የጤና መድህን አጋግሎት መሆኑ ተገልጿል!! በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ፣የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ…
Read more

ሳምንታዊ የህረተሰብ ጤና አደጋዎች ውይይት ተካሄደ ፡፡

ሳምንታዊ የህረተሰብ ጤና አደጋዎች ውይይት ተካሄደ ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና ማስተባበሪያ ማዕከል በወባ በሽታና በሌሎች የጤና ጉዳዮች ሳምንታዊ ውይይት አድርጓል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በመድረኩ እንደገለጹት የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር በ32% ጭማሪ ማሳየቱን በመጠቆም በቀጣይ ጊዜያት ወቅቱን ታሳቢ…
Read more

በሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ የ”40″ኛ ሣምንት “EOC” በመምሪያ ደረጃ ተገመገመ።

ሪፖርቱ በአቶ እንዳለ በኩል ሰፋ ባለ መልኩ የቀረበ ሆኖ ከወባ አንፃር የ40ኛ ሣምንት 1591 case ሆኖ ከአምናው ተመሳሳይ ሣምንት ከነበረው 1955 ቁጥር አንፃር የመቀነስ አዝማምያ ያለ ቢመስልም እንኳ ከባለፈው ሣምንት (39ኛ) አንፃር 1121 የነበረ ስለነበር 466 የጨመረበት ሁኔታ እንዳለ ተብራሮቷል። ‎ ‎ከፍተኛ የወባ ቁጥር የታየባቸው ሶሮ 169(10.6%), ጎምቦራ 150(9.4%), ሾኔ 144 ሆኖ ከወባ አይነት (species)…
Read more

በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጤና ጽህፈት ቤት የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሙዱላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

“በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጤና ጽህፈት ቤት የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሙዱላ ከተማ እየተካሄደ ነው። የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ “በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት በ2017 ዓ.ም ዓመታዊ በሙዱላ…
Read more

ከ15 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ሬዝደንት አማካሪዎች ቴክኖሎጂ በትምህርት ስርዓቱ ስለሚካተትበት ሁኔታ እየመከሩ ነው

ከ15 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ሬዝደንት አማካሪዎች በአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን በፍጥነት ለመለየት፣ ለመመርመርና ለማከም እንዲቻል ዘመን ያፈራው ቴክኖሎጂ በትምህርት ስርዓቱ በሚካተትበት ሁኔታ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው። የፊልድ ኢፒዲሞሎጅ ስልጠና ፕሮግራም ለህብረተሰብ ጤና አገልግሎት የጀርባ አጥንት መሆኑን የገለፁት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ቀጣዩ የአፍሪካ ጤና አገልግሎት በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ የኢፒዲሞሎጅ ባለሙያዎች…
Read more

የቻይና የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያየ

በዛሬው እለት ከቻይናው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን (Chinese Disease Control and Prevention Authority /CDCPA/) የመጡ የልኡካን ቡድን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉ መስኮች ላይ መክረዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እንግዶቹን በተቀበሉበት ወቅት ከዚህ ቀደም በሁለቱ ሀገራት ግንኙነቶች የተደረጉ የሰው ሀይል አቅም ግንባታና ስልጠና እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ተግባራት አመርቂ ውጤቶች ማስገኘታቸውን…
Read more

12ኛው አመታዊ የ COECSA ኮንግረስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

“የተርሸሪ የአይን እንክብካቤን በ COECSA ሃገራት ማሳደግ፡ ጊዜው አሁን ነው” በሚል መሪ ቃል 12ኛው የምስራቅ፣ መካከለኛ እና ደቡብ አፍሪካ የዓይን ህክምና ኮሌጅ (COECSA) ኮንግረስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ኮንግረሱ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ ባለሙያዎችን፣ የአይን ጤና ባለሙያዎችን እና ሰልጣኞችን ጨምሮ ከ40 በላይ ከሚሆኑ ሃገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎችን በማሰባሰብ በአፍሪካ የአይን ህክምናን ማሳደግ ላይ ምክክር ያደርጋል።…
Read more

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ወር አፈጻጸም እና ሳምንታዊ የEOC ግምገማ ተካሄደ፤

ነሀሴ 15/2017 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ወር አፈጻጸም እና ሳምንታዊ የEOC ግምገማ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርቱ በልማት እቅድ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ጽጌ የቀረበ ሲሆን ሳምንታዊ የEOC ሪፖርት በድንገተኛ በሽታዎች አሰሳ እና ቅኝት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ነስረዲን ኑርዬ አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በግምገማ መድረክ የመምሪያው ኃላፊ ዶ/ር ሸምሱ…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሂዷል

በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ የወባ ጫናን ጨምሮ ሌሎች 36 በሽታዎች ላይ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ። የቢሮዉ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይ/ ዳይ/አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የዚህን ሳምንት ቅኝት ሲያብራሩ በሳምንቱ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀምና የግንዛቤ ስራዎችን በማጠናክር የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት አንፃር መቀነሱን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ወልደሰንበት ገለፃ የወባ በሽታ…
Read more