Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Author: admin

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወረርሽኝ መልክ የሚነሱ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወረርሽኝ መልክ የሚነሱ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ በዛሬው ዕለት በተደረገው ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ተገልጿል ፡፡ ውይይቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በጋራ የመሩት ሲሆን ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ሆነው…
Read more

የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ በሥሩ ከሚገኙ ወረዳዎች ለተወጣጡት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በ Malaria case & Foci investigation response ዙሪያ ስልጠና መስጠቱን ገለፀ

በዞኑ ሥር ባሉት ወረዳዎች ለሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በክላስተር ደረጃ በሺንሽቾና በዳምቦያ ከተማ የተሰጠው ስልጠና የወባ በሽታ ቅኝትና አሰሳ ስራ በዕዉቀት ላይ ተመስርቶ በመስራትና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ሁሉንም ማህበረሰብ ክፍሎች ከበሽታው ለመከላከልና እንዲሁም የማህበረሰብ ንቅናቄዎችን ለማጠናከር አጋዥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወጋየሁ ወርቅነህ ሥልናዉን አስመልክቶ እንደተናገሩት…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ግብረ-መልስ ግምገማ ተደረገ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ግብረ-መልስ ግምገማ ተደረገ። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ደይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንዲሁም የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች በተገኙበት በወራቤ ከተማ አፈጻጸሙ ተገምግሟል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ደይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን የድንገተኛ…
Read more

ሁለት ራስ ቅል ያለው ልጅ ተወለደ::

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ራስ ቅል ያለው ልጅ በሰላም ተገላግላለች። በሆስፒታሉ የህጻናት ህክምና ክፍል ሃላፊ ዶክተር ባሳዝን ጣሰው እንደገለጹት፤ በሆስፒታሉ አንዲት እናት ሁለት ራስ ቅል ያለውን ህጻን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ ተገላግላለች። የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ወላዷ ከአንገቱ በታች በኩል የተያያዘ ሁለት ራስ ያለው ሆኖ የተወለደው ሕፃን ስድስተኛ ልጇ…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር ከግሎባል ፈንድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የወባ ላቦራቶሪ ማይክሮስኮፒ ምርመራ እና የጥራት ቁጥጥር ማረጋገጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር ከግሎባል ፈንድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የወባ ላቦራቶሪ ማይክሮስኮፒ ምርመራ እና የጥራት ቁጥጥር ማረጋገጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡የወባ ጫና ያለፉት በርካታ ዓመታት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች እጅግ ከፍተኛ መሆኑ በተለያዩ መረጃዎችና ጥናቶች መወቅ ይቻላል፡፡ ይህ የወባ ጫና በተለይም…
Read more

የድንተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስርአትን ይበልጥ በማጠናከር በማህበረሰቡ ላይ የተከሰቱና ሊከሰቱ የሚችሉ ጤና እና ጤና ነክ አደጋዎችን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ፤

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ክስተቶች፣ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ የጤና ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የድንተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስርአትን ይበልጥ ማጠናከር ተገቢ መሆኑን ነዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስባበሪያ ማዕከል /EOC/ በሳምንታዊ የአፈፃፀም ግምገማዉ ላይ የተብራራዉ ፡፡ በክልሉ ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት፣ወራት…
Read more

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝና ሌሎች የማህበረሰብ ጤና ስጋቶች እንዳይስፋፉ የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰራባቸው መሆኑ ተገልጿል፤

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝና ሌሎች የማህበረሰብ ጤና ስጋቶች እንዳይስፋፉ የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰራባቸው መሆኑ ተገልጿል፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ባደረገዉ የምክክር መድረክ አፅንዖት ሰጥቶ ከመከረባቸው ጉዳዮች መካከል በአንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተውን የኩፍኝ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች…
Read more

Ato Mamush Hussein

በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ወረርሽኞች የማህበረሰብ የጤና ስጋት እንዳይሆኑ መደበኛ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ወረርሽኞች የማህበረሰብ የጤና ስጋት እንዳይሆኑ መደበኛ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማዉን በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በዚሁ ጊዜ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ግዛቸው ዋሌራ…
Read more