Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማሕበረሰብ ጤና አደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማሕበረሰብ ጤና አደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከሉ ኢንሲደንት ማናጀር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለጹት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center – PHEOC) ክልሉ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ወጥ በሆነ መልኩ በየሳምንቱ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ሰርቬላንስ መረጃ በመተንትን የቅድመ ዝግጅት ፤ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ስራዎች በመገምግሞ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ተቋማት እና መዋቅሮች በመለየት የጤና አደጋዎች ከስታንዳርድ በላይ ሞት ሳያስከትሉ እየተቆጣጠረ መሆኑ ገልጸው የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል በአዲስ መልክ መደራጀቱን ተከትሎ በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የአስቸኳይ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማእከል ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ እና ይህንንም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማዕከሉ መጠናከር አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ወንበሮች ፤ ጠረጰዛዎች ፤ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና ፕሪንተር እና የዲጂታላይዜሽን መሳሪያዎች ድጋፋ ማድረጉን በማመስገን ኢንስቲትዩቱ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች እና የሚመለከታቸው አካላት የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከሉ በተቀመጠለት ስታንዳርድ ለማደራጀት የበኩላቸው አስተዋጾኦ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *