
በዓለም አቀፍ ደረጃ መጋቢት 24 በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የሚከበረው የፓርኪንሰን በሽታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን የጤና ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የፓርኪንሰን ፔሽንትን ሰፓርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የማህበሩ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ተከብሯል።
በግንዛቤ ማስጨበጫው መድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ዶ/ር ህይወት ሰለሞን በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንዳሉት የፓርኪንሰን በሽታ የአንጎላ ነርቭ ስርዓትን የሚጎዳና ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ በሽታ እንደሆነ አንስተው እጅ ወይም አካል መንቀጥቀጥ፣ የእንቅስቃሴ መዘግየት/መዛል፣ የጡንቻ መጠንከር፣ የሚዛን መዛባት/መውደቅ፣ ድብርት ወይም ጭንቀት፣ የእንቅልፍ ችግር፣ ማሽተት አለመቻል እንዲሁም የድካም ስሜት የበሽታው ምልክቶች መሆናቸውን ገልጸው የበሽታው ምልክቶቹ የሚታይባቸው ስዎች በፍጥነት ወደ ህክምና መሄድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አክለውም በጤና ሚኒስቴር ከፓርኪንሰን በሽታ ተያይዞ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ከተሰሩ ስራዎችም መካከል የነርቭ ህመም እና ፓርኪንሰን በሽታ ጨምሮ የህክምና መመሪያ ማዘጋጀትና በጤና ፓሊሲው ውስጥ ትኩረት እንዲሰጠው መደረጉ፣ ለታካሚዎች ተደራሽና ፈጣን ምርመራና ህክምና እንዲያገኙ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ እንደሚገኝ፣ የመድኃኒትና የሪሀቢሊቴሽን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ እንዲሁም በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየተከናወኑ እንደሚገኝ አብራርተው የታካሚዎችን ችግር ለመቅረፍና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ ላለው ለፓርኪንሰን ፔሽንትን ሰፓርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የፓርኪንሰን ፔሸንትን ሰፓርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ መስራችና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኒውሮሎጂ ሙሁራን ተገኝተው እለቱን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB


