Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Category: EOC

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል መጎልበት በጤናው ሴክተር የማይንገራገጭ ስርዓት ለመገምባት ወሳኝ ነው አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ኃላፊ

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል መጎልበት በጤናው ሴክተር የማይንገራገጭ ስርዓት ለመገምባት ወሳኝ ነው አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ኃላፊ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል ሳምንታዊ የአፈጻጸም ግምገማ ከዞንና ከልዩ ወረዳዎች ጋር በበይነ መረብ አካሂዷል። በሳምንቱ 64,307 ሰዎች የወባ በሽታ ምርመራ ማድረጋቸውንና 21,158 ሰዎች የወባ በሽታ ተገኘቶባቸው ህክምና ማግኘታቸውን የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።…
Read more

የወባ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ

ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር በሚገኘዉ በሺንሽቾ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወባ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩም የወባ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወባ በሽታ ምልክቶችና መተላለፊያ መንገዶች እንዲሁም የበሽታዉ መከላከያ መንገዶች ዙርያ ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ የተሰጠ መሆኑን ተገልጿል።

የወባ በሽታ ወረርሽኝ አሁን ካለበት ስርጭት ደረጃ ከፍ እንዳይል የሁሉም አመራር እና የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

ጥቅምት 5/2017 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ሳምንታዊ የ (EOC)የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምለሽ አሰጣጥ ሳምንታዊ አፈፃፀምና ወቅታዊ የወባ በሽታ ስርጭትን አስመልክቶ ውይይት በዛሬው እለት ተካሂዷል። የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምለሽ አሰጣጥ እና የማህበረሰብ ጤና አደጋዎችና የወባ ወረርሽኝ ምላሽ መስጠት ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩም በዞናችን ስር በሚገኙ በሁሉም መዋቅሮች የወባ ወረርሽኝ በተከሰተባቸዉ ቀበሌያት የበሽታውን ሥርጭት…
Read more

መጪውን ክረምትና የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የወረርሽኝ ስጋቶችን ለመመከት የሚያስችል የቅድመ መከላከል እንዲሁም የቅኝትና ምላሽ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ገምግማ ማካሄዱን የማዕከላዊ ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ገልጿል። ሳምንታዊ የክንውን ሪፖርት እና የቅኝት ምላሽ አሰጣጥ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ። 7,065 የወባ በሽታ ኬዝ ሪፖረት መደረጉን እንዲሁም የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት በ23/% ጭማሪ ማሳየቱን እና በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ አየጨመረ መምጣቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል። እንደ ክልል…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህ/ጤ/ኢ/ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ተግባራትን ገምግሟል ።

የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ በሳምንቱ ዉስጥ የተከናወኑ የቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ተግባራት ቀርበው ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ። አቶ አገኘዉ ፀጋዬ የቢሮው ጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሳምንቱን ሪፖርት ሲያቀርቡ በዚህ ሳምንት 5176 የወባ በሽታ መከሰቱን ጠቁመዋል ። በክልሉ በሳምንቱ ከምባታ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ 604 ሰዎች ወይም 27 በመቶ በወባ በሽታ ከፍተኛ ቁጥር…
Read more

በኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ወቅት ነባራዊ ሁኔታዎች እና የተሰጡ ምላሾች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉ ተገለጸ።

ኳሊቲ ሄልዝ ኬር አክቲቪቲ ፕሮጀክት ከሚደግፋቸው የሀዲያ ዞን 3 ወረዳዎች እንዲሁም ከጉራጌ ዞን 1 ወረዳ ላይ የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተከናወኑ ተግባራት አንዲሁም የተሰሩ የምላሽ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው እለት በሆሳዕና ከተማ መደረጉን የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ገልጿል። የክትባት አገ/ት ጥራትና ደህንነትን የማሰ ጠበቅ ፋይዳና አገ/ት አሰጣጥ ላይ ያሉ የአፈጻጸም ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችል መግባባት ላይ…
Read more

የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ እየተከሰተ ባለው የጎርፍ አደጋ ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መደበኛ የወረርሽኞች መቆጣጠሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center – EOC) የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ሳምንት ( WHO week 19) ግምገማ ተደርጓል፡፡ ሳምንታዊ የተጠቃለለ የበሽታዎች ክስተት፣ ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በክልሉ እየተከሰተ ያለው የጎርፍ አደጋ አሳሳቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በድንገት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን አስመልክቶ ሰፋ…
Read more

በበየሳምንቱ ለሚሰበሰቡ መረጃዎች ትረጉም እየተሰጠ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ተገለፀ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ጤና መምርያ 45ኛ ሳምንት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል(EOC) ዉይይት የመምርያው ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በተገኙበት በቀን 05/09/2016 ዓ.ም ያካሄደ ሲሆን፡- በሳምንቱ በቅኝት ስር ሪፖርት ከሚደረጉ በሽታዎች እንደ ወባ እና የምግብ እጥረት፤ ከመረጃ ጥራት ጋር ተያይዞ እንደ ሪፖርት ምሉዕነት እና ወቅታዊነት እንዲሁም ደግሞ በመረጃ ቅብብሎሽ ዙሪያ በስፋት ሪፖርት በመምርያው…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) የ15ኛው ሳምንት (Epi-week 15/2024) ሪፖርት ግምገማ አካሄደ::

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) የ15ኛው ሳምንት (Epi-week 15/2024) ሳምታዊ የቅኝት ሪፖርት የገመገመ ሲሆን በበይነ መረብ በቀረበው ሪፖርት የዞንና የልዩ ወረዳዎች ተሳታፊዎች አስተያየት የሰጡ ሲሆን የታዩ ጠንካራና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ለይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ደይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም…
Read more

በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መደበኛ የወረርሽኞች መቆጣጠሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center – EOC) የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ሳምንት ( WHO weeke 10 ) ግምገማ በቀን 11/07/2016 ዓ/ም ባደረገው ውይይት በክልሉ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።…
Read more