የካቲት 9/2017 ዓ/ም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የመጀመሪያ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 14-17/2.017 ዓ/ም ድረስ ቤት ለቤት እንደሚሰጥ ተገለፀ
በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡ በክልል ደረጃ ለሚገኙ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ቡታጅራ ከተማ የአድቮኬሲ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡…
Read more
