Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Author: admin

CERPHI

በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ::

በሚቶ ወረዳ በመንግስትና ማህበረሰብ ትብብር የተገነባውና ለማህበረሰቡ መድሃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የሚጠበቀው የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ተመርቋል የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ኡስማን ሱሩር እና በሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ…
Read more

የካቲት 9/2017 ዓ/ም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የመጀመሪያ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 14-17/2.017 ዓ/ም ድረስ ቤት ለቤት እንደሚሰጥ ተገለፀ

በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡ በክልል ደረጃ ለሚገኙ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ቡታጅራ ከተማ የአድቮኬሲ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡…
Read more

ከየካቲት 14-17/2017 ዓ.ም በዘመቻ የሚሰጠውን የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ በትኩረት እየሰራ ነው የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ

የዘመቻውን ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዕቅድ ሰነድ እና የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ከመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ጎን ለጎን ተቀናጅተው የሚከናወኑ ተግባራት የቆልማማ እግር ልየታ፣ ምንም ክትባት ያልተከተቡ ህጻናት ልየታ፣ የምግብ እጥረት በሽታ ልየታ እና የማዐጤመ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ላይ ተግባራትን በልዩ ትኩረት የመፈጸም ጉዳይ ላይ ሁሉም…
Read more

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ክልላዊ የመረጃ ቅመራና ትንተና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተደርጓል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ክልላዊ የመረጃ ቅመራና ትንተና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተደርጓል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ክልላዊ የመረጃ ቅመራና ትንተና ማዕከል መመ ስረቱን ተከትሎ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴንን ጨምሮ ከክልሉ…
Read more

በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሆሣዕና ከተማ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሆሣዕና ከተማ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል። የከቲት 04/2017 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢ/ክ/ጤ/ቢሮ የህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ (nOPV2) ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ ከዞንና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ጤና ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ሥልጠና መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ…
Read more

“ኢትዮጵያ ጠንካራና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመዘርጋት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቁርጠኝነት ትሰራለች።”

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮዽያ አባል የሆነችበት የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ 156ኛው ስብሰባ በስዊዝርላንድ ጀኔቫ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤን በማጎልበት፣ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል። ሚኒስትሯ በማከልም ለዘላቂ የጤና መሰረት ስርአት፣ የሀገር ዉስጥ የህክምና ግብዓት ምርትን ለማሳደግ…
Read more

አመራሩ ሙሉ ትኩረቱን የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለበት – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

( ሆሳዕና፣ የካቲት 2/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎች ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት አጠቃላይ ስራዎች አፈጻጸምን በጽህፈት ቤታቸው ገምግመዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት አመራሩ ሙሉ ትኩረቱን የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለበት…
Read more

የሕብረተሰብ የጤና አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱና ፈተና እየሆኑ ስለመጡ የጤና ስርዓቱ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ሊኖረው ይገባል፡- የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ::

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት10ኛውን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ፎረም ”የማይበገር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስርዓት ለብሄራዊ ጤና ደህንነት” በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ዛሬ እዚህ የደረስነው እንደሃገር በተለያዩ ጊዜያት ሲፈትኑን የነበሩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በጋራ ምላሽ በመስጠት ነው፤ ለዚህ ደግሞ በየደረጃው የሚገኙ የጤናው…
Read more

የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከስተ በኋላ የመልሶ ምልከታ ወርክ ሾፕ መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን ቅኝትና ምላሽ ከማጠናከር አኳያ እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል በርካታ ተግባራቶች እየተከናወነ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ገልጿል። በክልሉ ስር ከሚገኙ ዞንና ወረዳዎች ለተውጣጡ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ሰጪ ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ ተጀምሯል። የማ/ኢት/ክ/ጤ/ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ…
Read more

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ልማት ህብረት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ያላቸዉን ተሳትፎ የሚያጠና የጥናት ስራ በተመለከተ በዛሬ ዕላት ለመረጃ ሰብሰቢዎች በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊሲ ጥናት ምርምር በጋራ በመሆን ” Level of Women Development Union Engagement on Health Extension programm at Central Ethiopia Region” በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል የሴቶች ልማት ህብረት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ያላቸዉን ተሳትፎ የሚያጠና የጥናት ስራ በተመለከተ በዛሬ ዕላት ለመረጃ ሰብሰቢዎች በሆሳዕና ጤና ሳይንስ…
Read more