Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Author: admin

የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በማዕከላዊ ኢትዮጺያ ክልል በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቤት ለቤት ጉብኝት ይሰጣል!!

የፖሊዮ በሽታ በአገራችን ለብዙ ህጻናት ህመም፣ የአካል ጉዳትና ሞት ምክንያት ከሆኑት በሽታዎች መካከል አንዱ ነዉ። የፖሊዮን በሽታ መከላከል የሚቻለው ህጻናትን በመደበኛና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን ክትባት ስናስከትብ ነው!! በመሆኑም የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከየካቲት 14-17/2017 ዓ.ም ድረስ በቤት ለቤት ጉብኝት ይሰጣል፡፡ስለሆነም ህፃናት ከዚህ ቀደም የፖሊዮ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም በዘመቻው እንዲከተቡ…
Read more

በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሳይንሳዊ ምርምር በማስደገፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ

(ሆሳዕና፣ጥር 24/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በባህላዊ መድሀኒት ጥናት ላይ በትብብር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ውል ስምምነት ተፈራረሙ የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ እንደገለጹት ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የህዝቡን የጤና ችግሮች መፍታት የሚችሉበትን እድል መፍጠር ይገባል ብለዋል። በክልሉ ካሉ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር በጤና…
Read more

Ato Samuel Darge and Ato Ashenafi Petros

የጤና ኤክስቴንሽኖች የተሃድሶ ስልጠና መስጠት መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

የጤና ኤክስቴንሽኖች የተሃድሶ ስልጠና መስጠት መጀመሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። ከክልሉ ስልጤ፣ ጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ እና ሀላባ ዞኖች ከተመረጡ ወረዳዎች ለተውጣጡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል። የቢሮው ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ በመግለጽ በበጀት ዓመቱ ከታቀዱ ተግባራቶች አንዱ…
Read more

Ministry Of Health

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ____________ የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና ራሺያ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸው ትብብር በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅ…
Read more

የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ የድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስ ሪፖርት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አስሩም መዋቅሮች የተሰማራው የድጋፋዊ ክትትል ቡድን ግብረ መልስ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የውይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የድጋፍ ክትትል ቡድኑ አባላት በድጋፍ ክትትሉ ወቅት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡና በቁርጠኝነት ለመወጣት ላዳረጉት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል። በድጋፍ ክትትሉ በጉድለት ለተለዩ ጉዳዮች የአጭርና የረዥም ጊዜ የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል EOC ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል።

ጥር 20/2017 ዓ/ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል EOC ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል። የቢሮው ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ከለላው አቻምየለህ የሳምንቱን ሪፖርት ሲያቀርቡ ባለፈው ሳምንት የነበረው የወባ ጫና በዚህ ሳምንት 2.1% ጭማሪ አሳይተዋል ብሏል። ባለፈው ሳምንት 6685 የነበረው በዚህ ሳምንት…
Read more

ጥራቱን የጠበቀ የምጥና የወሊድ አገልግሎት በመስጠት በእናቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ሞት ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ

ጥራቱን የጠበቀ የምጥና የወሊድ አገልግሎት በመስጠት በእናቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ሞት ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ (ጥር19/2017 )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጤናማ እናትነት ወር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደገለጹት የጤናማ እናትነት ወር መከበር አብይ ዓላማ የእናቶችንና የህፃናትን ጤና በማሻሻል ጤናማ ህብረተሰብን ለመፍጠር ያለመ…
Read more

ወባን ለማስወገድ አዳዲስ ስልቶች እና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በሚቻልበት መንገድ ላይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በመድረኩ እንደተናገሩት ስብሰባው የወባ መድሃኒቶችን ወጪ ለመቀነስ እና ወባን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማጎልበት የሚስችሉ ስልቶች ላይ ለመወያየት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። የወባ በሽታን ለመከላከል የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊነት እና ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ዶ/ር መቅደስ የተናገሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ተቋሞችን ማጠናከር እና የመከላከል ስራዎችን ማጎልበት ከጥረታቸው ግንባር ቀደም መሆን እንዳለበት…
Read more

Metheorology

በቀጣይ 10 ቀናት የሚኖረውን የበጋ ደረቅ ርጥበት በመጠቀም ምርት መሰብሰብ ይገባል- ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል የሚኖረውን የበጋ ደረቅ ርጥበት በመጠቀም አርሶ አደሮች ሰብል የመውቃትና ምርት የማጓጓዝ ስራ እንዲያከናውኑ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው የትንብያ መግለጫ እንደጠቆመው በቀጣይ 10 ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ፀባይ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሌሊትና በማለዳ ቅዝቃዜ እንደሚኖር…
Read more

የአፍሪካ ህብረት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ እንድታጤነው ጠየቀ::

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ መልሳ እንድታጤነው ጠይቀዋል፡፡ ሙሳ ፋኪ አሜሪካ ከድርጅቱ አባልነት ለመውጣት መፈለጓ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ ውሳኔውን መለስ ብሎ በማጤን በአባልነቷ ትቀጥላለች የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) መስረታ ላይ ቀደምት እና…
Read more