Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Author: admin

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ወረርሽኝ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ላይ የንቅናቄ ስራዎች ልዩ ዕቅድ ላይ በሆሳዕና ከተማ ውይይት እየተደረገ ነው

ሆሳዕና ሚያዝያ 08/2017ዓ.ም የዕለቱ የክብር እንግዳና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ የወጣቶች ክንፍ በበጀት ዓመቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተግባራት የተመሩበት አግባብ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች የተመዘገበቤት አግባብ ነው ያለው። ብልፅግና ፓርቲ በትውልድ ሽግግር የሚያምን ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ቀድሩ የወጣቶች ክንፍ የወጣቶች ድምፅ የመሆን…
Read more

የክልሉ የጤና መረጃ አስተዳደር ስርዓትን ለማሻሻል ዲጂታል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በክልሉ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህብረተሰብ ጤና መረጃ ጥንቅር እና ትንተና ላይ ያተኮረ ስልጠና ለኢንሰሸቲትዩቱ ባለሙያዎች በሆሳዕና መስጠት ተጀምሯል፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የመረጃ ስርዓትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ማድረግ መረጃ በአንድ ቋት በማከማቸት እንደ አገር ውሳኔ ለመስጠት ያገለግላል ብለዋል ፡፡…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ላስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም ከጤና ሚኒስተር እውቅና አገኘ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ላስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም ከጤና ሚኒስተር እውቅና አገኘ ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ በማህበረሰብ ተሳትፎና በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታን በተሻለ በመተግበር ላስመዘገባው አፈጻጸም ከጤና ሚኒስተር እውቅና አገኘ ፡፡ ቢሮው እውቅና ያገኘው የጤና ሚኒርተር የዘርፉን አፈጻጸም መድረክ በጅማ ከተማ ባካሄደው መድረክ ላይ ነው ፡፡ በመድረኩ የጤና ሚንስተር አመራሮችና ባለሙያዎች፣…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዩጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማሙሽ ሁሴን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለስቅለትና ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የማዕከላዊ ኢትዩጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማሙሽ ሁሴን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለስቅለትና ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዓሉን ስናከብር መላው ህዝባችን ራሱን ከተላላፊ እና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ሊጠብቅ ይገባል በተለይም ወቅቱ ዝናባማ በመሆኑ ከወባ፣ ከኮሌራ፣ ከኩፍኝ በሽታዎች ራሱን ለመጠበቅ በየአካባቢው ከሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክር መቀበል፤ አጎበር በአግባቡ መጠቀም፣…
Read more

በኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ላይ እየታየ ያለውን መዘናጋት ለማስቀረት ጉዳዩን ቀዳሚ አጀንዳ በማድረግ መስራት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ላይ እየታየ ያለውን መዘናጋት ለማስቀረት ጉዳዩን ቀዳሚ አጀንዳ በማድረግ መስራት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) አሳሰቡ (ሆሳዕና ሚያዚያ 3/2017) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ…
Read more

ከ338 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ህገ-ወጥ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ በሰጡት መግለጫ ከ338 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ህገ-ወጥ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች መያዛቸውን ገልጸዋል። ከህወጥ ድርጊቱ ጋር በተያያዘ 19 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባለፈው ሳምንት…
Read more

የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ።

የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ አቀረበ። የክልሉ ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን በጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ላይ ለጤና ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የነበረው የ3 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተጠናቋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊና ጤናና…
Read more

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣዉን ኤችአይቪ ኤድስና ቫይራል ሂፓታይተስን ለመከለል እና ለመቆጣጠር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣዉን ኤችአይቪ ኤድስና ቫይራል ሂፓታይተስን ለመከለል እና ለመቆጣጠር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ለቢሮዉ ሰራተኞች በወቅታዊ የኤችአይቪና ቫይራል ሄፓታይተስ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቪ ሆስፒታል ዉይይት አድርገዋል ፡፡ አቶ አለማየሁ ጌታቸው በጤና ቢሮ የኤችአይቪ ኤድስ እና ዘርፈ ብዙ ዳይሬክቶሬት…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሂዷል የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ በሳምንቱ ዉስጥ የተከናወኑ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ። የቢሮው ጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘሪሁን ደሞዜ የሳምንቱን ሪፖርት ሲያቀርቡ ባለፈው ሳምንት 4801 የወባ በሽታ መከሰቱን ጠቁመዉ በዚህ…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ የተለያየ ድጋፎች ተደረገለት።

የማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ የተለያየ ድጋፎች ተደረገለት። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚንስቴር እና አጋሮች ያገኛቸውን የኤሌክትሮኒክስ እና የናሙና ማመላለሻ ቁሳቁሶች ድጋፍ፣ ለክልል ላቦራቶሪዎች አድርጓል። በርክክቡ ወቅት፣ የጤና ሚንስቴር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ጀነራል ዳይሬክተር ዶክተር ሳሮ አብደላ፣…
Read more