
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አስሩም መዋቅሮች የተሰማራው የድጋፋዊ ክትትል ቡድን ግብረ መልስ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የድጋፍ ክትትል ቡድኑ አባላት በድጋፍ ክትትሉ ወቅት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡና በቁርጠኝነት ለመወጣት ላዳረጉት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል።
በድጋፍ ክትትሉ በጉድለት ለተለዩ ጉዳዮች የአጭርና የረዥም ጊዜ የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት ወደ ስራ መግባት ይገባል ያሉት አቶ ሳሙኤል እንደ ክልል እና አንደ ዞን እንዲሁም እንደ ልዩ ወረዳ የሚከናወኑ ተግባራትን በመለየት ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ስልቶችን በመንደፍ ለመፈጸም በሚወርደው ግብረ መልስ መሠረት ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በምርጥ ተሞክሮ የተለየቱን ተግባራቶች ወደ ሌሎች የሚሰፋበትንና የሚቀመርበትን ሁኔታ የማመቻቸት እና በጥንካሬ የተለዩ ጉዳዮች ደረጃቸውን እንደጠበቁ የማስቀጠል ሂደቶችን በትኩረት ማከናወን እንደሚገባም ገልጸዋል።
ድጋፋዊ ክትትሉ በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸውን ስራዎች በደንብ ያመላከተ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ሳሙኤል በዕቅድ ላይ ተመስርቶ ተግባራቶችን መፈጸም አበረታች ለውጦችን ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑንም አስረድተዋል።
የድጋፋዊ ክትትሉ ስራ በታችኛው መዋቅር ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ደካማ እና ጠንካራ ጎኖችን ነቅሶ ያወጣ እና በጤናው ሴክተር እንዲመዘገብ ለታቀደው ውጤት አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን የቀረቡ ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
በነበራቸው የድጋፍ ክትትል ቆይታ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ያሳዩት ቁርጠኝነት በቀጣይ ለሚከወኑ ተግባራት ተነሳሽነትን የፈጠረ መሆኑን የድጋፍ ክተትል ቡድኑ አባላት የገለጹ ሲሆኑ በቀጣይ ትኩረት በሚደረግባቸው ጉዳዮች ላይ ሁሉም የድጋፍ ክትትል ቡድኑ አባላት የበኩላቸው ድርሻ ለመወጣት መግባባት ላይ ተደርሷል።
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ


