Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወቅታዊ ተግባራት ላይ ውይይት ማድረጉን ገለፀ

ጥር 14/2017

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወቅታዊ ተግባራት ላይ ውይይት ማድረጉን ገለፀ

በክልሉ በዚህ አመት የተከናወኑ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች እና ወረርሽኞች ቁጥጥር ላይ ከፍተኛ መሻሻል የታየበት እና ይህም ተግባሩ በቅንጅት በመመራቱ የተነሳ የመጣ ውጤት ሲሆን በተለይ ከክትባት ጥራት እና ተደራሽነት እንዲሁም ክትባት ያልወሰዱ እና ያቋረጡ ህፃናትን ለይቶ የመከተብ ስራ (Big-Catch Up Campaign) በሁሉም የክልሉ ዞኖችን ልዩ ወረዳዎች በመከናወኑ ከክትባት ጋር በተያያዘ ይከሰቱ የነበሩ ወረርሽኞች መቀነስ ማሳየታቸው ተነስቷል። በውይይቱም በቀጣይ በክልሉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች የሚከናወነውን የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት ቅድመ ዝግጅት ተገምግሟል። ውይይቱን የመሩት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ሲሆኑ በማጠቃለያቸውም የተጀመሩ መልካም የሆኑ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አንስተው በተለይ የወባ በሽታ ላይ ከላይ እስከታች በተደረገው ርብርብ የመጣው ለውጥ እንዳለ ሆኖ አሁንም በሽታው የህብረተሰቡ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አንስተው በክልሉ ወረዳዎችን እና የጤና ተቋማትን ታሳቢ ያደረገ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስርአት እና የላብራቶር አገልግሎትን ትኩረት ያደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ ማከናወን እንደሚገባ አንስተው ከዚሁ ጎን ለጎን በክልሉ በቀጣይ የሚሰጠውን የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻን በጠንካራ ቅድመዝግጅት መምራት እንደሚገባ እቅጣጫ ተቀምጧል። በመጨረሻም በኢንስቲትዩቱ የተጀመሩ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን ያለበትን ደረጃ በመገምገም ማጠናከርያ ሃሳቦችን በማንሳት ውይይቱ ተጠናቋል።

መረጃው – የማ/ኢ/ክ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *