Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አገኘ::

ጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አገኘ

____

አሲስት ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ወደ ሁለት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ሺ ሶስት መቶ ዶላር እና ሪች አናዘር ፋውንዴሽን ደግሞ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የህክምና መሳሪዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የተሻሻለው የጤና ፖሊሲ በሽታን ከመከላከል ባሻገር ህመምተኛን አክሞ ማዳን ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ጠቅሰው፤ ድጋፉ በሀገራችን ያለውን የጤና ስርዓት አገልግሎት እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ፍሬህይወት ከአሲስት ኢንተርናሽናል የተገኙት ወደ 41 የሚሆኑ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የተገዙት የታካሚዎች ክትትል ማድረጊያ እና የመተንፈሻ ስርዓት ማገዣ መሳሪያዎች በተመረጡ ስምንት አጠቃላይ ሆስፒታሎች አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረግ አንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ትምህርት መርጃ እንደሚያግዙም ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብድርቃድር ገልገሎ በበኩላቸው የህክምና መሳሪያዎቹ ድጋፍ አገራችን ከአለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የአሲስት ኢንተርናሽናል ፕሬዚደንት ራልፍ ሰድፊልድ /Ralph Sudfeld CEO/President at Assist International በዓለም ዙሪያ ካሉ ለውጥ ፈጣሪዎች ጋር በመተባበር ላለፉት ዓመታት የዜጎችን ጤና የሚደግፉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ አመላክተው፣ መሰል ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን የጤና ስርዓት ለመደግፍ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎችም የጤና ሚኒስቴር ምቹ ሁኔታ እየፈጠረላቸው እንደሆነ በማመስገን ተናግረዋል፡፡

ከሪች አናዘር ፋውንዴሽን የተገኙት የኒውሮሰርጂካል ማይክሮስኮፖች የጭንቅላት፣ ነርቭ እና ህብለ-ሰረሰር ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ቀደም ብሎ ለተለዩ ሆስፒታሎች እንደሚከፋፈልና በሪፈራል ለመታከም ወደ አዲስ አበባ የሚመጡትን ህሙማን በአከባቢያቸው የህክምና አገልግሎት ለማግኘት እንደሚያስችላቸው ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *