Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማ/ኢ/ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የHIV ቅኝት እና ምላሽ ተግባራት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተደርጓል።

Ato Leggese and Alemayehu

የማ/ኢ/ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የHIV ቅኝት እና ምላሽ ተግባራት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተደርጓል።

ጥር 9/2017 ዓ.ም

የማ/ኢ/ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የHIV ቅኝት እና ምላሽ ተግባራት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተደርጓል።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ ባስተላለፉት መልዕክት የHIV AIDS በሽታን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር ጠንካራ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም እንደ ሀገር የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የበለጠ ርብርብ ማድረግ እነደሚገባ ተናግረዋል።

አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ከማግኘትና የህክምና አገልግሎት ከማስጀመር እንዲሁም ከእናት ወደ ልጅ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ የሚሰሩ ስራዎችን ከማጠናከር አንጻር ልዩ ቱኩረት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል ።

በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት በCDC የHIV case surveillance አስተባባሪ የሆኑት አቶ አገኘሁ ፀጋዬ የ6 ወሩን የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ በHIV Case surveillance ማዕቀፍ የተካተቱ እና ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባቸው 36 ተቋማት ቢኖሩም በባለፉት 6ወራት ሪፖርታቸውን በአግባቡ በREDCap እያስገቡ ያሉት ጤና ተቋማት ግን 32ቱ ብቻ መሆናቸውን የቀረበው ሪፖርት ያመላክታል።

ከመረጃ ጥራት ጋር በተያያዘ አቶ ሀብታሙ ሀ/መስቀል ረፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከመረጃ ጥራትን ከማስጠበቅ አኳያ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮቸ እንዳሉ ጠቅሰው በቀጣይ መፈታት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

በመጨረሻም የቀረቡትን ሪፖርት መነሻ አድርጎ ወይይት የተደረገ ሲሆን ከውይይቱም ተሳታፊዎች በተሰጠው አስተያየት የHIV Case Surveillance ፕሮግራም አዳዲስ የቫይረሱን ተጠቂዎችን ለማግኘት፤ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ለማስቻል እና የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ገልፀው የፕሮግራሙ አፈፃፀም ላይ የሚታዩ ክፍቶችን ለማሻሻል የበኩላቸውን አስተዋፅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የመዝጊያ ውይይቱን የመሩት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ እና የዘርፈ-ብዙ የHIV/AIDS መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አለማየሁ ጌታቸው ሲሆኑ ሀላፊዎቹ የHIV ቫይረስ ስርጭትን ዜሮ ለማድረግ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *