
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል
ኢንስቲትዩቱ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ተግባራት ላይ የማኔጅመንት አካላት እና የዘርፉ ሰራተኞች በተገኙበት የተገመገመ ሲሆን ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።
የማ/ኢት/ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ
የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማሻሻል የክልሉን የላብራቶሪ ስራዎች በማሻሻል ተደረሽነቱን ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
የወባ በሽታ በቀጣይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ተገቢዉን የቅድመ ጥንቃቄ ስራን በማጠናከር እንዲሁም ቀድሞ ቅኝት በማድረግ እና በመተንበይ መዘጋጀት ይገባልም ብለዋል ።
አቶ ሳሙኤል አክለውም የምግብ እጥረት በሽታን ለመከላከልና የከፋ ጉዳት ከማምጣቱ በፊት ቀድሞ ለመቆጣጠር ችግሩ የሚከሰትባቸውን አካባቢዎች ፈጥኖ በመለየት የልየታ ስራዎች በማጠናከር ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
እንደ አጠቃላይ የዳይሬክቶሬቶቹ አፈፃፀም የሚበረታታ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊዉ በቀጣይ ይህን ውጤት አጎልብቶ ለማስቀጠል ከሌሎች ዳይሬክተሮች ጋር በመቀናጀት እና በመናበብ በርካታ ስራዎችን መፈጸም እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
የቢሮው የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው በ2017 በጀት ዓመት በግማሽ ዓመቱ ወሳኝ የሚባሉ ተግባራት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን ገልፀው በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
እንደ አቶ ማሙሽ ገለፃ የክልሉን ላብራቶሪ በማደራጀት እና የሆሳዕናን ቅርፍ ደግሞ ይበልጥ በማጠናከር የዜጎችን የጤና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
በተያዘዉ በጀት ዓመት በ6 ወራት ውስጥ ውስን በሆነ የሰው ሀይል የህብረተሰቡን የጤና ችግር ሊቀርፍ የሚችል ጥናትና ምርምር የተደረገ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ማሙሽ በቀጣይ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሰው ሀይልና የበጀት ድጋፎች የሚሳለጡበትን ሁኔታ ከማመቻቸት አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል ።
የታችኛውን መዋቅር በተለያዩ ጊዜያት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እያበቁ እንደሚገኙ ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ስልጠናው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ።
በአጠቃላይ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት ውስጥ በዘርፉ ስር በሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ የተገመገመ ሲሆን ወጤቱን ለማስቀጠል ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል ።
የማ/ኢት/ ክልል ጤና ቢሮ

