Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ክልሉ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተረከባቸውን 15 አምቡላንሶች ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች አስረከበ::

ክልሉ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተረከባቸውን 15 አምቡላንሶች ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች አስረከበ

(ሆሳዕና፦ ጥር 5/2017) የጤናውን ስርዓት የሚያፋጥኑ አምቡላንሶችን ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ማስረከቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ

በርክብክብ ወቅት ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ አምቡላንሶቹ የእናቶችንና ሕፃናትን ሞት ከመቀነስ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች አዲስ የተሰጣቸውንም ይሁን ከዚህ በፊት ያሉትን አምቡላንሶችን በወሊድ ወቅት እናቶችን ቶሎ ወደ ጤና ተቋማት በማድረስና ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰት የሰው ልጆችን ሕይወት ለማዳን አገልግሎት ብቻ ሊያውሉ ይገባል ነው ያሉት።

ለክልል የተሰጠውን 15 አምቡላንሶች የጤናውን ስርዓት የሚያሳልጥ መሆኑን ገልፀው አምቡላንሶችንም የክልሉን ነባራዊ ሁኔታን ባገናዘበና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማዳረስ ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

ከአምቡላስ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነም ገልፀዋል።

በጤና ተቋማት አምቡላንስ መኖር አገልግሎቱን የተሻላ የሚያደርግ በመሆኑ አምቡላንሶቹን ለታለመለት ዓለማ ብቻ እንዲውል ኃላፊዎቹ ቅርብ ክትትል እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

አምቡላንሶችን ርክብክብ ያደረጉ ዞኖችና ልዩ ወረዳ ጤና መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንደገለፁት አምቡላንስ የጤና ሴክተር ትልቁ ተግባር ማሳክያ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል።

አምቡላንሶችን ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል እናቶች እና ሕፃናት በአንቡላንስ እጥረት ምክንያት የሚያጋጥመውን ሞት በመቀነስ የጤናው ስርዓት እንደሚያሳልጡም ተናግረዋል።

በአድነው አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *