Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማ/ኢት/ክ/ሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል በሳምንታዊ እና ወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።

ማስተባበርያ ማዕከሉ እንደ አዲስ ባደራጀው EOC የወባ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ያለበት ሁኔታ፣ የምግብ እጥረት፣ እንዲሁም በሌሎች የጤና ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት ዙርያ ውጤታማ ስራዎች መስራታችው እና ተጨባጭ ውጤት መገኝቱ፣ለዚህም የጤና ተቋማት ለወባ ህክምና ዝግጁ መደርጋችው፣የቤት ለቤት ቅኝት፣አሰሳ እና የታመሙ ሰዎችን ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ መደርጉ እና መሻሻሎች መታየታቸው ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የወባ ጫና መቀነስ ማሳየቱን የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን የወባ ምርመራ አቅምን ከፍ በማድርግ እና የምርመራ ቁጥርን በመጨመር እንዲሁም ህብረተሰቡን ያሳተፈ የወባ መከላከልና የመቆጣጠር ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል የወባ በሽታ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራው ትጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለው የስርዓተ ምግብ ልየታ አገልግሎት ማሻሻል፣ የግብዓት አጠቃቀምና ክትትል ስራን ማጠናከር በጤናው ሴክተር ቀጣይነት ያለው የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራን በማጎልበት ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የወባ በሽታ ዳግም የማህበረሰቡ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ብርቱ ርብርብ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የዞኖች እና ልዩ ወርዳዎች የሕብርተስብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከላት በሳምንታዊ ውይይቱ ላይ በZoom በመሳተፍ ወባን ጨምሮ ሌሎች የህብርተሰቡን የጤና ስጋቶች ከመከላከል እና ከመቆጣጠር ጋር በተሰሩ ስራዎች ላይ አስተያየታቸውን ስተዋል።

የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስ በየደረጃው እየተደረገ ያለው ርብርብ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ እና የወባ ጫና ከፍ ብሎ የሚታይባቸው የክልሉ አካባቢዎች የተጠናከር የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን መተግበር እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የማ/ኢ/ክ/መ/ጤ/ ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *