የጤናውን ሴክተር ተግባር በጥራት እና በፍታሀዊነት ተደራሽ ለማድረግ አጋር ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለጸ።
አጋር ድርጅቶች እና ቢሮው በቅንጅት በሚከናውኗቸው ተግባራቶች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
የዜጎችን ጥራት ያለው እና ፍትሀዊ የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ ከምንጌዜውም በላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገልጿል።
በጤናው ሴክተር ተፈጻሚ የሚደረጉ ተግባራትን ለማሳለጥ የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበትና በቅንጅት ሊሰሩ ይገባልም ተብሏል።
በጤናው ሴክተር ጥራት ያለው የጤና አገል/ት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ የአጋር ድርጅቶች ሚና ትልቅ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በየደረጃው ላሉ የጤና ባለሙያዎች የዓቅም ግምባታ ስልጠናዎችን በመስጠት የህክምና መገልገያ መሳርያዎችን በማሟላት፣ የመድሃኒት አቅርቦት ላይ የተለመደውን ትብብር በማድረግ ሁሉን ዓቀፍ ድጋፎች እንዲደረጉም ተጠይቋል።
የእናቶች እና የህፃናት ህመምና ሞት ለመታደግ እንዲሁም ሁሉ አቀፍ የጤና ተግባራትን ለማሳለጥ በትንሽ ድጋፍ ብዙ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ተመላክቷል።
በቀጣይ በማንኛውም ልማታዊ ስራዎች ተቀራርቦ እና ተናቦ መስራት እንደሚገባ ያወሱት የግብረ ሰናይ ድርጅት አካላት ለተለያዩ የጤና አገልግሎት ወደ ታች የሚወርዱ የስራ ቁሳቁሶች ለታለመለት ዓላማ እንዲዉሉ በባለቤትነት መንፈስ ክትትል መደረግ እንዳለበት አስረድተዋል ።
የቴክኒካል ወርክንግ ግሩፕ እና ፓርትነር ፎሮምን በየግዜዉ ማጎልበት፣ እቅዶቻችንን የጋራ ማድረግ፣ግንኙነታችንን ይበልጥ በማጠናከር የነበሩ ድጋፎችን አጠናክሮ ለማስቀጥል ተቀራርቦ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል።
በቀጣይ ቢሮውን በሚደግፍበት አንኳር ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ