Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የተደራጀ የጤና ልማት ሰራዊት በመጠቀም የወባ በሽታን መከላከል እንደሚገባ የስልጢ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ!

የተደራጀ የጤና ልማት ሰራዊት በመጠቀም የወባ በሽታን መከላከል እንደሚገባ የስልጢ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ!

ሐምሌ 21/2016 የስልጢ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን

የስልጢ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የተደራጀ የጤና ልማት ሰራዊትን በመጠቀም የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎች በማፋሰስና በማዳፈን ትንኝ እንዳይራባ ማድረግ በሚሉ መሪ ሀሳቦች ከዘርፉ ባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ወቅቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የወባ በሽታ ወርሽኝ ለመከላከል የተሰሩ ስራዎችንና በቀጣይ እየተባባሰ ያለውን የወባ በሽታ ለመከላከል የሚያስችሉ ስልቶችን እንዲሁም ህብረተሰቡ የበሽታውን መንስኤና መከላከያ መንገዶችን በመለየት እራሱን እና ወገኑን መከላከል በሚኖርበት ሁኔታ ላይ የተኮረ ሰነድ በጽ/ቤቱ ባለሙያ በአቶ ተስፋዬ አለሙ እየቀረበ ሲሆን ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት ውይይት እንደሚያደርጉበትና የቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *