Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ኢንስቲትዩት መረጃዎችንና ምላሽ ስራን የሚያስተባብሩ ማዕከላትን በማቋቋም የወባ ስርጭትን ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ኢንስቲትዩት መረጃዎችንና ምላሽ ስራን የሚያስተባብሩ ማዕከላትን በማቋቋም የወባ ስርጭትን ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ከሚዲያዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ መረጃዎችንና ምላሽ ስራን የሚያስተባብር ማዕከላትን በማቋቋም የወባ ስርጭትን ለመቀነስ እየሰራ ነው።

ማዕከላት በክልሉ ሰባቱም ክላስተሮች መቋቋማቸውን በመግለጽ ወባን ጨምሮ ሌሎችም ወረርሽኞችን ጭምር መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ሀሳብ የሚንሸራሸርበት መረጃ የሚጋራበትና ሀብት የሚፈላለግበት ማዕከላት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የወባ ስርጭት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በሀገር ብሎም በክልሉ በስፋት መከሰቱንና በወባ የማይታወቁ አዳዲስ አከባቢዎች ጭምር ስርጭቱ እንደታየባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በክልሉ የወባ ስርጭት የ2016 ዓ.ም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጻር 44 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን አቶ ማሙሽ ተናግረው ስርጭቱን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሰፋፊ የንቅናቄ መድረኮች መፍጠር፣ የቅኝት ስራዎችን ማጠናከር፣ የህክምና ተቋማትን በግብዓትና በሰው ሀይል ማደራጀት ከተሰሩ ስራዎች መካከል መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በክልሉ የወባ ስርጭትን ለመቀነስ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ በመጠቆም ሁሉም ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *