የማህበረሰቡን ንቃተ ጤና ከፍ የማድረግ ስራዎችን በማጠናከር የግልና የአካባቢ ንጽህና ተግባራትን በአግባቡ ማሳለጥ ይገባል ተባለ።
የተጠናከረ እና ለወረረሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓትን በመገንባት ፍትሀዊ እና ጥራት ያለው የጤና አገ/ት ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ገልጸዋል።
ጽዱ ኢትዮጲያን እውን ለማድረግ ባለፉት ጊዜያት የንቅናቄ ስራዎችን በመስራት የዞኑ አመራሮች እንዲቀላቀሉ መደረጉን የገለጹት አቶ ወንድሙ የግልና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ 85% በሽታን መካከል ከመቻሉም በላይ ጊዜንና አላስፈላጊ ወጪዎችን በማስቀረት ለሀገር እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል።
እንደ ዞን ባለፉት ጊዜያትም የተጠናከረ የግልና የአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ስራ በመሠራቱ ዞኑ የተለያዩ ወረርሽኞች ሰለባ አለመሆኑን ያስገነዘቡት ሀላፊው በዞኑ 153 ጤና ተቋማት 176,922 አባ ወራዎች 127 ት/ቤቶች መኖሩን በማውሳት የሴቶች አደረጃጀቶችንና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ተጽእኖ ፈጣሪ አካላትንና የተገኙ ምቹ አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ በአግባቡ በመስራት 87 ቀበሌያት 18ቱን የጤና ኤክ/ን ፓኬጆች አሟልተው ሞዴል መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ የሁሉም ዓይነት መጸዳጃ ቤት ሽፋን 100% የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ሽፋን 70% መሆኑንና እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ሙሉ ዞኑን ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ የማድረግ ስራዎች በመከናወን ላይ መገኘታቸውን እንዲሁም የግልና የአከባቢ ንጽህና አጠባበቅ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እና ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ የሆኑ ቀበሌያት ወደኋላ እንዳይመለሱ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ወንድሙ አክለው ገልጸዋል።
የቤተሰብ ጤና ክብካቤ አገ/ት እንደዞን 2012 ዓ.ም መጀመሩን የጠቀሱት ሀላፊው የተለያዩ ጤና ባለሙያዎችንና ጤና ኤክ/ሽን ባለሙያዎችን የያዘ ሆኖ በዱራሜ ከተማ ላሎ እና ዘራሮ ቀበሌያት እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሀደሮ ከተማ በቀጠና በቀበሌ እና በመንደር ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን በማመላከት ይህንን ተግባር በአግባቡ በማሳለጥ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሱትን የጤና ጉዳት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶችን በማስቀረት ረገድ ጉልህ ፋይዳ ማበርከቱን አስገንዝበዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ የመድሀኒት እጥረት ችግሮችን ለመቅረፍ የቀይ መስቀል መድሀኒት ቤቶችን እና የማህበረሰብ መድሀኒት ቤቶች ተሰርተው ችግሩ የሚፈታበት ሁኔታ በዱራሜ ከተማ የተመቻቸ ቢሆንም ወደ ሌሎች ከተሞች የማስፋት ስራዎች ተጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል።
የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ