የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የአደጋዎች ቅኝት የማህበረሰብ ጤናና ድንገተኛ መከላከል የ9ወራት አፈጻጸም ገምግሟል።
የልዩ ወረዳው ጤና ጽ/ቤት የአደጋዎች ቅኝት፣ የማህበረሰብ ጤናና ድንገተኛ መከላከል የ9 ወራት አፈጻጸም የአራቱ ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የPHEM ተጠሪዎች፣ የጽ/ቤቱ ማኔጅመንቶችና ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን ተግባሩን ገምግሟል።
በዚህም የአደጋዎች ቅኝት የ9 ወራት አፈጻጸም፣ ህብረተሰቡን በጤና አደጋ መከላከል ተግባር ላይ ባለቤት ከማድረግ፣ ወረርሽኝን ከመከላከል፣ የእናቶችና ጨቅላ ህጻናትን ሞት ሪፖርት ከማድረግ፣ ከሪፖርት ጥራትና ወቅታዊነት፣ የጤና ኬክስቴንሽኖች ድጋፍና ክትትል ከማድረግ አንጻር አፈጻጸሙ ቀርቧል።
በተጨማሪም ሪፖርትን ገምግሞ ከመላክ፣ የወባ፣ የቲቢ፣ የኮሌራ፣ የኩፍኝ፣ የምግብ እጥረትና ሌሎችንም በሽታዎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር የተከናወኑ ተግባራት በዘጠኝ ወሩ አፈጻጸም ተዳሰዋል።
በቀረበዉ የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ በርካታ በጥንካሬ የሚገለጹና የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን ባለድርሻ አካላቱ ያነሱ ሲሆን በቀጣይም ከቲቢ ልየታ፣ ሪፖርት ገምግሞ ከመላክና ከመናበብ፣ የወባ በሽታን ከመከላከል፣ ሪፈር ከማድረግ፣ በሁሉም የጤና ተቋማት በዘርፉ መስተካከል አሉባቸው በተባሉት ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ወራት በትኩረት እንደሚሰሩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ተናግረው የልዩ ወረዳው ጤና ጽ/ቤት በየዘርፋ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
በመጨረሻም የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀይ ኑርሀሰን እንደተናገሩት በልዩ ወረዳው እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ስርጭትና የኩፍኝ በሽታ ምልክቶች እንዳይባባሱ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች የበለጠ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የህብረተሰቡን የጤና አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራትና ተግባቦት ላይ በባለቤትነት በራሱ የመከላከል ልምድ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባ አቶ አብድልሀይ ጠቁመው በጤና ተቋሙ በኩል ቢሻሻል በተባሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸው በቀጣይ ቀሪ ወራቶች ለተግባራቱ ትኩረት በመስጠት በዘመቻ ተግባሩ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካል በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
በልዩ ወረዳው ጤና ጽ/ቤት በኩል ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአፈጻጸም ግምገማ ተጠናቆ በቀጣይ አስር ቀናት የሚሰሩ የዘመቻ ስራዎች ላይ አቅጣጫ በመስጠት ተጠናቋል።
ለቀ/ል/ወ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ዘገባ
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ