Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጤና ሚንስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ለሀብረተሰብ ጤና ላብራቶር አገልግሎት የሚውሉ የጂን ኤክስፔርት ማሽን ድጋፍ አደረገ፡፡

ጤና ሚንስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ለሀብረተሰብ ጤና ላብራቶር አገልግሎት የሚውሉ የጂን ኤክስፔርት ማሽን ድጋፍ አደረገ፡፡

የጤና ሚንስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባር በከፍተኛ ወጪ የገዛቸውን የጂን ኤክስፔርት ማሽኖችን በማዕከላዊ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማት ላብራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ ማሽኖችን በድጋፍ ማግኘቱን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ድጋፉም እንደ አገር ቲቢን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የታቀዱ የስትራቴጂክ ዕቅዶችን ለማሳካት ክፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ያወሱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በተለይም በአሁን ጊዜ የሳንባ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ከመለየት አልፎ ለቲቢ ህክምና ከሚሰጡ መድኃቶች ውስጥ ፊቱን መድሃኒቶችን ጭምር ለይቶ የሚያሳይ ከመሆኑም በለይ እጅግ የዘመነ ዓለም የደረሰበት የቲቢ ምርመራ ዘዴ ሲሆን በማይክሮስኮፕ በሚታየው የምርመራ ዘዴ በተለያየ ምክኒያት ልፈጠር የሚችለውን የባክቴሪያው የመለየት ስህተት የሚያስቀር በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

በሌላ መልኩ የበሽታ መከላከያ አቅም ማነስ ምክነያት በአክታ ውስጥ ውስን ባክቴሪያ ቢኖር እንኳን መለየት የሚችል ሲሆን፤ የአክታ ናሙና መስጠት ለማይችሉ ህጻናት ቲቢን ከሰገራ ናሙና መመርመር መቻሉና በተጨማሪም ከሳንባችን ውጪ ሌሎች የሰውነታችንን ክፍል የሚያጠቀውንም ቲቢን ከተለያየ የሰውነት ክፍል ፈሳሽን በመውሰድ መመርማር የሚያስችል ነው ።

በመጨረሻም ማሽኖቹ በቅርብ ግዜ ውስጥ ሥራ ለማስጀመር የኢንስታሌሽንና የሥራ ማስጀመሪያ ሥልጠና እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን ማሽኑ መስጠት ያለበትን አገልግሎት በአግባቡ መስጠት እንድችል የጤና ተቋማት፤ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት የከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት እና የዞን ጤና መምሪያ ማናጀመንት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለማሽኖቹ ምቹ የሥራ ክፍል በማመቻቸት፤ በቂ የመሰረተ ልማት አገልግሎት እንዲኖር ማስቻል፤ ማሽኖቹን በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባ ገልፀው ማሽኖቹ ከተቋም ውጪ ያሉትንም አጎራባች ጤና ተቋማትም ጭምር በናሙና ቅብብሎሽ ሰንሰለት ለሚመጡ ናሙናዎችም የነጻ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይህንንም ሥራ በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ አጽኖኦት ሰጥተው በቀጣይም ተጨማሪ ማሽኖች በሁሉም የክልሉ ከፍተኛ ጤና ተቋማት ለማዳረስ እንደሚሰራ አንስተዋል።

ምንጭ- የማእከላዊ ኢትዮጲያ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *