Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለማቋቋም እንዲሁም ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የመስተዳደር ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለማቋቋም እንዲሁም ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የመስተዳደር ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩቱ ቀድሞ በነበረው ክልል መቋቋሚያ ደንብ የነበረው ቢሆንም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንደ አዲስ የተዋቀረ ክልል እንደመሆኑ ክልላዊ አወቃቀሩንና ባህሪውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ደንቡን በጥልቀት አይቶ ለመገምገም ነው የመጀመሪያ ዙር ውይይት እየተደረገ ያለው፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ውይይቱን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የኢኒስቲትዩቱ አራት ዋና ዋና ተልዕኮዎችን ማለትሞ የወረርሽኝ ቁጥጥርና የጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ላይ ክትትል ማድረግ፣ የላቦራቶሪ አገልግሎትን በማሻሻል አለም አቀፍ ዕውቅና ያለው እንዲሆን ማስቻል ፣ የጤና ምርምር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራትን ማጠናከር እንዲሁም የጤና መረጃዎችን ወደ አንድ ቋት በማሰባሰብ አስፈፃሚ አካላት ለውሳኔ እንዲጠቀሙት ማስተግበር ነው ብለዋል ፡፡

ይህንንም ለማስተግበር ደንብ እና መመሪያ ወሳኝ በመሆናቸው ነው ኢኒስቲትዩቱን ለማቋቋም በወጣው ደንብ ላይ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ የሆነው፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክትር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ለማቋቋም እንዲሁም ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የመስተዳደር ምክር ቤት ያወጣው ረቂቅ ደንብ ያቀረቡ ሲሆን በመመሪያውም

በተመረጡ የጤናና እና የስነ-ምግብ ችግሮች ላይ ምርምር በማድረግ፣ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ በተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ ውጤታማ በሆነ የድንገተኛ የህብረተሰብ የጤና ችግር መከላከል፣ ቁጥጥር እና እንዲሁም የላቀ ጥራቱ የተረጋገጠ የህክምና ላቦራቶሪ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ጤና ማሻሻል እንዲቻል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቱዩት ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ስለ መገኘቱ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ አድረገዋል፡፡

የኢኒስቲትዩቱ ከፍተኛ ሀላፊዎችና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል እና ምክትል ቢሮ ሀላፊው አቶ አብረሀም በውይይቱ ላይ በመገኘት፣ በረቂቅ ደረጃ የወጣውን ደንብ በጥልቀት በማየት ያልተካተቱ ነጥቦች እንዲካተቱና ጉድለቶች እንዲታረሙ ውይይቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *