Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር ከግሎባል ፈንድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የወባ ላቦራቶሪ ማይክሮስኮፒ ምርመራ እና የጥራት ቁጥጥር ማረጋገጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር ከግሎባል ፈንድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የወባ ላቦራቶሪ ማይክሮስኮፒ ምርመራ እና የጥራት ቁጥጥር ማረጋገጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የወባ ጫና ያለፉት በርካታ ዓመታት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች እጅግ ከፍተኛ መሆኑ በተለያዩ መረጃዎችና ጥናቶች መወቅ ይቻላል፡፡ ይህ የወባ ጫና በተለይም በነፍሰጡር እናቶች በህጻናት እንዲሁም በሌላ በሽታ የተጠቁና የተፈጥሮ በሽታ መከላከያ አቅም እጥረት ያለባቸውን ህሙማን ለሞት የሚዳረግ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለዚህም ይህንን የወባ ጫና ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ ከሚደረገው የወባ መከላከያ መንገዶች መካከል ዋነኛው ጥራቱን የጠበቀ የምርመራ አገልግሎት ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡
በመሆኑም በጤና ተቋማት ደረጃ የሚሰጠውን የወባ ምርመራ አገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ የሠለጠነ እና ብቁ የሰው ኃይል፤ ያልተቆራረጠና ጥራቱን የጠበቀ የምርመራ ግብዓት፤ ጥራቱን የጠበቀ የምርመራ ማይክሮስኮፕ እጅግ በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ በመሆኑም በተደጋጋሚ በተደረገው የጤና ተቋማት ድጋፋዊ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም በመልሶ ምልከታ የውጫዊ የጥራት ቁጥጥር አተገባበር ላይ በተለይም ከሪኤጄንቶች አጠቃቀምና የወባ ተህዋስን የማወቅ እና በዓይነት የመለየት ችግሮች ጎልቶ የወጣ ክፍተት በመሆኑ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ችግሩ ጎልቶ ከሚታይባቸው መዋቅሮች ላይ ከሚገኙ ከ120 የጤና ተቋማት ለተውጣጡ 120 የላራቦራቶሪ ባለሙያዎች በአራት ዙር የንድፈ ሀሳብና የተግባር ሥልጠና ለስድስት ተከታታይ ቀነት ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች ስለ ሥልጠናው አሰጣጥ አስተያየት በሰጡበት ወቅት በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲ ካገኙት ዕውቀት የበለጠ መሆኑንና የሥልጠናውም አሰጣጥም በአገር አቀፍ ደረጃ የአሰልጣኞች ሥልጠና በወሰዱ የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ከፍተኛ ኤክስፕርቶች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ድርጅት የተረጋገጡ የተግባር ማስተመሪያ ስላይዶችን በመጠቀም ሁሉንም የምርመራ ሂደቶች በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተሰጠ በመሆኑ ወደ ተቋማችን ስንመለስ ያልሰለጠኑ ባለሙያዎቻችንን የሥራ ላይ ሥልጠና በመስጠት የሚጠበቀውን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይረክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ባስተላለፉት መልዕክት በአገሪቱ ከሚገኙ ክልሎች መካከል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በርካታ ከህክምና ወጪ ያሉ የወባ መከላከል ሥራዎች ተጠናክረው እየተሰሩ ቢሆንም በየሳምንቱ በሚደረጉ የድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) በሚደረገው የሳምንታዊ ውይይት ችግሩ ጎልቶ የሚታይባቸው መዋቅሮች መኖራቸውን በመግለጽ;
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወባ እና ሌሎች ዋና ዋና ተላላፊ በሽታዎች የምርመራ ጥራትን ለማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ከአንድ ሳምንት በፊት በተደረገው የኢንስቲትዩቱ የስድስት ወር አፈጻጻ ግምገማ መድረክ ላይም በርካታ ባለድርሻ አካለት በተገኙበት የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት በተለይም ለአክርዲቴሽን በ3ኛ ደረጃ በሚገኙ ሆስፒታሎች፤ የደረጃ በደረጃ ላቦራቶሪ ጥራት አተገባበር የኮከብ ደረጃ ማግኛ በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፤ የአጠቃላይ የላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር አመራር በጤና ጣቢያዎች፤ እንድሁም የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር አተገባበር በሁሉም የጤና ተቋማት ለመተግበር አቅጣጫ መቀመጡን አውስተው ሰልጣኞች ሲመለሱ በቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት እንድተገብሩ እና ላልሰለጠኑት የሥራ ላይ ሥልጠና እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ደይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ግርማ ወንድሙም የወባ መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም ማስወገድ ሥራ ላይ የላቦራቶሪ ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ሥራ ያለፉትን በርካታ አመታት የለቦራቶሪ ባለሙያዎችን በሥልጠናና በሜንቴርሽፕ እንዲሁም በድጋፋዊ ክትትል ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ቢሆንም በተለይም የባለሙያ መልቀቅ፤ የግብዓት ዕጥረት፤ የሪኤጄንት ጥራትን ያለመጠበቂ፤ እንዲሁም የማይክሮስኮፕ ብልሽት እና የአያያዝ ጉድለት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች መኖራቸውን አውስተው እነዚህንና ሌሎች የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በጤና ተቋማት ላይ በሚተገበሩ የላቦራቶሪ ሪፎርሞች ላይ በቀጣይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስተውቀዋል፡፡
በሌላ መልኩ በሥልጠናው ማጠቃለያ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ጤናን ማጎልበት ደይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ፍስሃ ላዕመንጎ እንደ አገር የተቀመጠውን የወባ ማስወገድ ሥራን በክልሉ በሁሉም መዋቅር በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጻው ጥራት ያለው የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት አሰጣጥ ለሚደረገው የወባ ማስወገድ ሥራ የላቦራቶሪ ድርሻ የጎላ መሆኑን አንስተው ሰልጣኞቹ ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ በወረዳ እና በጤና ተቋማት ከሚገኙ የአመራር አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *