
*********:::::::::************
የ2018 የወረረሽኝ ስጋት ይሆናሉ ተብለው በተለዩ በሽታዎች ; የሚስፈልገው የግብኣትና በጀት ላይ ያሉት ችግሮች የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ በተገኙበት የጋራ ተደርጓል
አቶ ሞሳ ኢዶሳ በውይይቱ እንደገለፁት ጤናማ እና አምራች ዜጋ በማፍራት በልዩ ወረዳችን ደረጃ ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኝ በተለይም ወባ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ልዩ ትኩረት ሰቶ የሚሰራ በመሆኑ ዘርፉን ለመምራት አስፈላጊውን የበጀትና ሌሎች ድጋፎች እንደሚደረጎ አቶ ሞሳ ኢዶሳ በውይይቱ ገልፀዋል።
የጤና ፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አብድልሀይ ኑርሀሰን እንደገለፁት የማህበረሰብ ጤና አደጋ ቅድመ ዝግጁነት ላይ በጤና ስራ ጠንካራ ቅንጅትን የሚፈልግ በመሆኑ በቀበሌ ደረጃ ያሉ ባለድርሻዎችን በተለይም አመራሩን ና ባለሙያዎች በማሳተፍ የማህበረሰቡን ጤና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት መስራት እንደሚያስያፈልግ ጠቅሰዋል።
በውይየቱም በተቋሙና በዘርፉ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት እንዲሰራ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ አብራርተዋል።
ስለሆነም በ2018 በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ እንዲከናወኑ የታቀዱ ተግባራትን በስኬት ለመፈጸም የጤና ባለሙያው እና የአመራሩ ቅንጅታዊ ድጋፍና ተሳትፎ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ሀላፊው አክለው አስገንዝበዋል ።

