Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ሁለተኛዉ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓተ ጉባዔ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ብዙ ጠቀሜታ አለዉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

ሁለተኛዉ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓተ ጉባዔ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለዉ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በ ጉባዔው ከሌሎች ሀገሮች የምንማርበት እና እኛም ደግሞ ወደ ተግባር የተሸጋገርንበትን መንገድ ለሌሎች የምናሳይበት ነዉ ብለዋል።

በፈረንጆቹ 2021 በተደረገው የመጀመሪያው ጉባዔ ላይ ተሳታፊ የነበረችው ኢትዮጵያ፤ የምግብ ሥርዓት ጉዳይን በዕቅድ ውስጥ በማስገባት ልትተገብራቸው ቃል ከገባችባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ በዚህም በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም የተገኙ ዉጤቶችን በማስፋት በአሁኑ ወቅት ከ340 በላይ ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። ምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ለጤና ትልቅ ፋይዳ አለው ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ በሥርዓተ ምግብ ውስጥ ያለፈ ትውልድ ጤናማ እና ምርታማ እንዲሁም ትልቅ ውጤት ማምጣት የሚችል ነው ብለዋል።

ነገ በይፋ በአዲስ አበባ የሚጀመረዉ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ጉዳዮችን በስፋት የሚዳስስ ትልቅ ጉባዔ ነዉ ያሉት ዶ/ር መቅደስ ከዚህ አንጻር ከሌሎች ሀገሮች የምንማርበት፣ እንዲሁም እኛም ደግሞ ከቃላት ወደ ትግበራ የተሸጋገርንበትን መንገድ ለሌሎች የምናሳይበት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *