Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር ይገባል፡-ጤና ሚኒስቴር::

ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር ይገባል፡-ጤና ሚኒስቴር

**********

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ድጋፎች በመቀነሳቸው፣ ለጤናው ዘርፍ የሚውል ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በራስ አቅም ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ የሚመክር ዓውደጥናት ተካሂዷል።

በመድረኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ድጋፎች መቀነሳቸውን ያነሱት የጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ፤ ለዚህ መፍትሔው የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅምን መፍጠር ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ከመንግሥት ባሻገር ሲቪክ ማኀበራት ለጤናው ዘርፍ የሚያስፈልገውን የገንዘብ አቅም በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

መንግሥት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመሥጠት በጀት ከመመደብ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

እንደሀገር አቅም ያላቸው ከፍለው ሲታከሙ፣ አቅሙ የሌላቸው ደግሞ በነፃ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ የሚያስችል ሥራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል ሚኒስትር ድኤታው።

ከዓድዋ ድል እና ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ባልተናነሰ መልኩ በሀገሪቱ ሕክምናን ነፃ ለማድረግ መረባረብ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በአልጋነሽ ተካ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *