Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ላስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም ከጤና ሚኒስተር እውቅና አገኘ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ላስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም ከጤና ሚኒስተር እውቅና አገኘ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ በማህበረሰብ ተሳትፎና በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታን በተሻለ በመተግበር ላስመዘገባው አፈጻጸም ከጤና ሚኒስተር እውቅና አገኘ ፡፡

ቢሮው እውቅና ያገኘው የጤና ሚኒርተር የዘርፉን አፈጻጸም መድረክ በጅማ ከተማ ባካሄደው መድረክ ላይ ነው ፡፡

በመድረኩ የጤና ሚንስተር አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተገኙ ሀላፊዎች እንዲሁም የጤና አጋር ድርጅቶች ተገኝተዋል ፡፡

በመድረኩ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ክልሎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል ፡፡

የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ በስምንት ወራት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖታ ካርታን ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ንቅናቄ ከመንግስት ፣ ህብረተሰቡና ከባለሀብቶች ሀብት በማሳበሰብ የአጠቃላይ ጤና ኬላዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሻሻል ፣ የጤና ኬላዎች ግንባታ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አረጋግጧል ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ባከናወነው የንቅናቄ ስራዎቹ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ እንደ አገር 3ተኛ ደረጃ በመሆን እውቅና ማግኘት ችሏል ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የተሰጠውን እውቅና አቶ ፍስሐ ለዕመንጎ የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ተወካይና የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ተቀብለዋል ፡፡

እውቅናው ክልሉ ባለፉት ስምንት ወራት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ በመተግበር ፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ እና በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስቀጠል በቀጣይ ከዚህ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ መሆኑን አቶ ፍሰሀ ገልጸዋል ፡፡

ይህ ውጤት እንዲመጣ የቢሮ አመራሮች እና ማኔጅመንት በቅንጅት ለተግባሮች ልዩ ትኩረት በመስጠት በመመራቱ የተገኘ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልፃዋል ፡፡

ለመላው የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ቤተሰቦች እና አጋዦች እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *