
የካቲት 27/2017 ዓ/ም
የጤናው ዘርፍ ስራዎችን ለማሻሻል የሚደረጉ ድጋፎች ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንዲውሉ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ገለጹ ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስትር ያገኘውን የሞተር ሳይክሎችን ለዞኖች ፣ለልዩ ወረዳዎች እና ለጤና ቢሮ ተጠሪ ተቋማት ድጋፍ እና ርክክብ ተደርጓል ፡፡
በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት ቢሮዉ በተለያዩ ወቅቶች የታችኛውን መዋቅር የጤና ሴክተር ግቦች ለማሳካት አጋዥ የሆኑ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዉ ቢሮዉ በአጠቃላይ 56 ሞተር ሳይክሎችን ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች ለጤና ቢሮ ተጠሪ ተቋማት የርክክብ ስነ-ስርዓት አድርገዋል ፡፡
እንደ አቶ ሳሙኤል ገለፃ ከጤና ሚንስተር ከተሰጡት 56 ሞተር ሳይክሎች ዉስጥ 52ቱ ለዞን እና ልዩ ወረዳ መዋቅሮች መሰራጨቱን ገልጸው ጠቅሰው 4 ደግሞ ለክልሉ ተጠሪ ተቋማት ተደራሽ መደረጉን አመላክተዋል ።
ሀላፊዉ አክለዉም ለዜጎች ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የተሻለ ግብዓት እንዲያገኙ ለማስቻል የተደረገዉ ድጋፍ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልፀው አገልግሎት ለሚሰጡ አካባቢዎች በቀጥታ ተደራሽ እንዲሆን ያሳሰቡ ሲሆን
ሞተር ሳይክሉም ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲዉል ጨመምረው ገልጸዋል ፡፡
ድጋፍ የተደረጉት ቁሳቁሶች የክትባት ስራዎችን ለማጠናከር ፣ የተለያዩ ግብአቶችን ከወረዳ ወደ ጤና ጣቢያ እንዲሁም ከጤና ጣቢያ ወደ ወደ ጤና ኬላ ለማመላለስ፣ ከጤና ተቋማት ጋር ያለዉን የድጋፍና ክትትል ስራዉን ይበልጥ ለማጎልበት ፣ የወረርሽኝ በሽታዎችን ለመከላከል ሚናዉ የጎላ ነዉ ሀላፊዉ ብለዋል
ክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከጤና ሚኒስትር ያገኘውን ድጋፎቾች ለታችኛው መዋቅር የአምቡላንስ ፣የላብቶፖችና የሞተር ሳይክሎችን ድጋፎችን በተለያዩ ጊዜያት መደረጉን አቶ ሳሙኤል ጠቅሰዉ ለጤና ሚንስተርና እና ለአጋር ድርጅቶች የላቀ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል
በሸምሲያ አደም




