
በ4ኛው ዙር የኢትዮጽያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ትስስር መረጃን መሰረት ባደረገ ህክምና አገልግሎት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሆስፒታሎች የዋንጫ ፣ የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት በክልሉ ጤና ቢሮ አማካኝነት ተሰጥቷል ፡፡
ውድድሩ በግልጽ በተቀመጠ እና በገለልተኛ አካላት በተካሄደ ምዘና የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ሆስፒታሎች የተደረገ ሲሆን እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል ፡፡
ሽልማቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፣ የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል እና የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና በቢሮው ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ ተሰጥቷል ፡፡
ሽልማቱ በሶስት ዘርፎች ማለትም ከመሪ ሆስፒታሎች፣ ከአባል ሆስፒታሎች እንዲሁም ከወረቀት ነፃ አገልግሎት በመተግበር የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሆስፒታሎች የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በክልሉ ካሉ መሪ ሆስፒታሎች መካከል በተቀመጠ ግልጽ መመዘኛ በተካሄደ ምዘና አንደኛ ወራቤ ኮንፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፣ ሁለተኛ ቡታጅራ ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲሁም ንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምኘሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሶስተኛ በመውጣት የዋንጫ ፣ የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
ከአባል ሆስፒታቶሎች መካከል በሸኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንደኛ ፣ ቡኢ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሁለተኛ እንዲሁም ጦራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሶስተኛ በመውጣት የገንዘብ የዋንጫ የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነዋል ፡፡
በሶስተኛው ዘርፍ ተሸላሚ የሆኑ ሆስፒታሎች ደግሞ ከወረቀት ነጻ አገልግሎት በመተግበር የቻሉ ማለትም ወራቤ ኮንፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፣ ቡታጅራ ጠቅላላ ሆስፒታል ፣ ሀላባ ቁሊቶ ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲሁም በሸኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እውቅና ተሰጥቷል ፡፡
በመድረኩ የቡታጅራ ግራር ቤት ተሀድሶ ሆስፒታል በፕሮግራሙ ልዩ ተሸላሚ መሆን ችሏል ፡፡

