Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ትክክለኛና ጥራት ያለውን መረጃ መሰብሰብ ለጥናትና ምርምር ስራዎች ወሳኝ ነው ተባለ

(ሆሳዕና፦ የካቲት 27/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ውጤታማነትና የፋይናንስ አስተዳደር በሚል ርዕስ ለመረጃ ሰብሳቢዎች በወልቂጤ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል።

የአመራር አካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ እንደተናገሩት ትክክለኛ እና ጥራት ያለውን መረጃዎችን መሰብሰብ ለጥናትና ምርምር ስራዎች ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን በኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት በርካታ ተግባራትን ማከናወን የተቻለበት ፕሮግራም ነው ብለዋል።

የጤና አገልግሎት የአንድ ተቋም ተግባር ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቋማት በጋራ በመስራት የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ እና ከማስጠበቅ አኳያ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚገኙ ማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ አወንታዊ አስተዋጽኦ እየበረከተ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት አሰጣጥ የሚታየውን የውጤታማነትና የፋይናንስ አስተዳደር ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመጠይቁ መሰረት ትክክለኛ መረጃዎችን መረጃ ሰብሳቢዎቹ መሰብሰብ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

የሚሰበሰቡ መረጃ በቀጣይ ለሚደረገው ተግባር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ትክክለኛ፣ተጨባጭ እና ሚዛናዊ ሊሆን ይገባል ብለው ተሰብስበው የሚመጡ መረጃዎች የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የአመራር አካዳሚው ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካይረዲን ራመቶ የሀገራችንን ብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች የልህቃን አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ልህቃን በተለያዩ ጥናትን ምርምር ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ሊሰሩ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት በተፈለገው መልኩ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጠ እና ውጤታማነቱ በምን ደረጃ እንዳለ በክልሉ በሁሉም አካባቢ የተጣራ መረጃ ይሰበሰባል ብለዋል።

ሰልጣኞቹ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ውጤታማነትና የፋይናንስ አስተዳደር የሚታዩ ክፍተቶችን በሚገባ በመለየት ለቀጣይ ስራ ትክክለኛ መረጃዎችን በመሰብሰብ ለታለመለት ዓለማ ለማዋል በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ውጤታማነትና የፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና ተጫባጭ መረጃዎችን መሰብሰብ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል።

ትክክለኛና ጥራት ያለውን መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን ለሚመለከተው አካል የማድረስ ስራ እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

በአድነው አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *