Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ተላላፊ በሽታዎችን ከመከላከል አኳያ ክትባት ትልቁን ድርሻ የሚወስድ በመሆኑ በዘመቻ መልክ በሚሰጡ ተግባሮች ላይ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተመላከተ፡

በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ዙር የሚሰጠው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በቀቤና ልዩ ወረዳ ፍቃዶ ጤና ኬላ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በዚህ ወቅት እንዳሉት ሀገራችን የምትከተለው መከላከል ላይ መሠረት ያደረገው የጤና ፖሊሲ የፋውስ ህክምና መጨመሩን አንስተዋል፡፡

የህፃናትን ሞት ከመቀነስ አኳያ በጤና ዘርፎች ላይ የሚሰጠው ክትባት ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ያነሱት ኃላፊው ለዚህም የ7 ዓመት የጤና ልማትና እንቨስትመንት ዕቅድ ተግባራዊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዘመቻው እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የክትባቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አቶ አሸናፊ አንስተዋል::

ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ተቀናጅተው በሚሰሩ ተግባሮች ጎን ለጎን ክትባት ያልወሰዱ ህፃናትን የመለየት ሥራ መዘንጋት እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡

የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር ሞሳ ኢዶሳ በበኩላቸው ለዘመቻው ተደራሽነት መጠነ-ሰፊ ዝግጅቶች መደረጉን አንስተው፣ እስከ ዘመቻው ፍፃሜ የትግበራ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ለዘመቻው ውጤታማነት የወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ሚና የጎላ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የወረዳው ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድላሂ ኑርሀሰን ናቸው፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴንን ጨምሮ የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎችና ዳይሬክተሮች የልዩ ወረዳው የፊት አመራሮችና የስራ ሃላፊዎች የክትባት ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *