
11/2017 ዓ/ም
ወራቤ
በማዕከላዊ ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር በአቶ ማሙሽ ሁሴን አማካኝነት የተመራ የድጋፍ ቡድን ከየካቲት 14-17 ዓም እድሜአቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚሰጠውን የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ቅድመዝግጅት እና የማዕጤመ ተግባራት አፈፃፀም የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ እና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ሃላፊ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር እና የመምሪያው ማኔጅመነት በተገኙበት ግምገማ ተደርጓል ።
በወቅቱ ከክልሉ ድጋፋዊ ክትትል ቡድን በክትባቱ ቅድመ ዝግጅት እና የማጤመ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በተለይ ለክትባቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ከማሟላት÷ የቅስቀሳ እና የቅዝቃዜ ሰንሰለት ዝግጅት፤ የየህብረተሰብ ንቅናቄ ስራዎች ምን እንደሚመስል እና ለታችኛው መዋቅር ከክትባቱ ጋር ተያይዞ የተሰጠ ስልጠና በውይይቱ ትኩረት የተደረገበት ሲሆን የዞኑ የእስካሁን የማጤመ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ። በተነሱ ዋናዋና ተግባራት የእስካሁን የዙኑን እንቅስቃሴ ተጨማሪ ማብራርሪያ በዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን በኩል ሃሳብ ተሰጥቷል ።
በመጨረሻም የክልልኡ ጤና ቢሮ ም/ሃላፊ እና የህብረተስብ ጤና ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር የክትባት ዘመቻውን ጥራቱን በጠበቀ መንገድ መተግበር ፖሊዮን ለማጥፋት ለተያዘው ግብ ወሳኝ መሆኑን ለዚህ ደግሞ ቀሪ የቅድመዝግጅት ስራዎችን ታች ድረስ ወርዶ ማረጋገጥ እንደሚገባ እና ከማጤመ እና ሌሎች የቅንጅት ተግባራት ረገድ አዲስ አባል ማፍራት ላይ፤ የተሰበሰበ የማጤመ ገንዘብ ገቢ ማድረግ እና ድጎማ ያላስገቡ የዞኑ መዋቅሮች በአጭር ግዜ እንዲያስገቡ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል ።
የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት ወ/ር ነኢማ ሙኒር በበኩላቸው የፖሊዮ ክትባት ቅድመ ዝግጅት እና በአመራሩ ተሳትፎ መደገፍ ያሉባቸውን ተግባራት በማንሳት ከማጤመ ጋር በተያያዘም በፓርቲ መሪነት ተከታታይ ግምገማ እየተደረገበት ሲመራ መቆየቱን እና ቀሪ ስራዎችን በአጭር ግዜ መፈፀም እንደሚቻል አንስተዋል ።
በመጨረሻም ለድጋፍ ወደ ዞኑ የተሰማራው ቡድን የሚካሄደውን የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ቅድመዝግጅት እና የማዕጤመ ተግባራት እና ሌሎች ተግባራት ለመደገፍ ወደ ዞኑ ወረዳዎች ተሰማርቷል.።
የማእከላዊ ኢ/ያ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት



