
ከየካቲት 14-17/2017 ዓ/ም ለ4 ተከታታይ ቀናት ዘመቻው ይካሄዳል፡፡
በዘመቻውም ከ1 ሚሊየን በላይ አድሜያቸው 5 ዓመትና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በጤና ባለሙያዎች አማካይነት ክትባቱን እንደሚያገኙ ተመላክቷል፡፡
ቤት ለቤት በሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር ክልል አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ላይ የግብአት አቅርቦት ችግር እንዳይኖር ቅድመ ዝግጅት መደረጉ በገለጻው ወቅት ተበራርቷል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በገለጻው ወቅት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት ለዘመቻው ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
ሁሉም ባለድርሻ ለተግባሩ ውጤታማነት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ሳሙኤል አሳስበዋል፡፡
ለዘመቻው ውጤታማነት የጤና ባለሙያዎች አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ ናቸው፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው በክልሉ የሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ የዘመቻው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ
