Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ::

በሚቶ ወረዳ በመንግስትና ማህበረሰብ ትብብር የተገነባውና ለማህበረሰቡ መድሃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የሚጠበቀው የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ተመርቋል

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ኡስማን ሱሩር እና በሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ከድር መሀመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የዞኑ አስተባባሪ አካላት፣ የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር፣ ሌሎች የክልል የዞንና የወረዳ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *