Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

“ኢትዮጵያ ጠንካራና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመዘርጋት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቁርጠኝነት ትሰራለች።”

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

ኢትዮዽያ አባል የሆነችበት የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ 156ኛው ስብሰባ በስዊዝርላንድ ጀኔቫ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤን በማጎልበት፣ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።

ሚኒስትሯ በማከልም ለዘላቂ የጤና መሰረት ስርአት፣ የሀገር ዉስጥ የህክምና ግብዓት ምርትን ለማሳደግ ፣ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎትን ለማሟላት እና ብቁ የጤና ክብካቤ ሰራተኛን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች አጋር አካላትም ጥራቱ የተጠበቀ፣ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተያዘዉ ግብ እንዲሳካ ዘርፈ ብዙ ድጋፋቸዉን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ይህ መድረክ ሃገራችን ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ተሳትፎና ተቀባይነት በማጠናከር በጤና ዲፕሎማሲ ረገድ ከፍተኛ ሚና ለመጫወት የሚያስችል ሲሆን ወቅታዊ የሆኑ የዓለም አቀፍ ጤና አጀንዳዎች ላይ ለዓለም ጤና ጉባኤው የውሳኔ ምክረ ሃሳቦች እንደሚያቀርብም ይጠበቃል፡፡

በሃገራችን በኩል Strengthening National Capacity in evidence based decision-making for uptake and impact of norms and standards በሚል ርዕስ የቀረበው ረቂቅ ሰነድም ከ80 በላይ በሆኑ ሃገራት ድጋፍ ያገኘ ሲሆን በጤናው ዘርፍ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት የሚወጡ የህክምና እና የማህበረሰብ ጤና ስታንድርድና መመሪያዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ መልካም ዕድል እንደሚፈጥር ይታመናል፡፡

Website: moh.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *