
( ሆሳዕና፣ የካቲት 2/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎች ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት አጠቃላይ ስራዎች አፈጻጸምን በጽህፈት ቤታቸው ገምግመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት አመራሩ ሙሉ ትኩረቱን የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለበት ብለዋል።
በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመሩ ተግባራት ስኬታማ
ናቸው ብለዋል።
የስራ ባህልን ማሻሻል እና የቁጠባ አቅምን ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በበጀት አመቱ አስቀድሞ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመዋል።
በእቅድ ዝግጅት ወቅት ከፈጻሚው ጋር የጋራ መግባባት በመፍጠር ወደ ተግባር በመገባቱ የተሻለ ግንዛቤ መጨበጥ እንዳስቻለም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
አብዛኛው አመራር በስራ ላይ በመሆን ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።
ለስራ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን እያረሙ መሄድ አስፈላጊ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኑሮ ውድነትን ለማርገብ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ገበያውን ለማረጋጋት የሰንበት ገበያዎች እንዲስፋፉ የተደረገው ጥረት የተሻለ እንደነበርም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር የልማት እና የሰላም ስራዎች ላይ ማተኮር የአመራሩ ቀሪ ስራዎች ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመቀናጀት የጋራ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።
አመራሩ በሙሉ አቅሙ በመስራት በውጤት ላይ የተመሰረተ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የገቢ እና የስራ እድል ፈጠራን የህልውና ጉዳይ አድርጎ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የገቢ መሰረትን በማስፋት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከመደበኛ ስራ ውጪ አዳዲስ አሰራሮችን እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከተረጂነት ለመውጣት የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል።
ለስራ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመከታተል ማረም እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
ኮንትሮ ባንድ እና ህገወጥ ንግድን መከላከል እንደሚገባ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በመሬት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራር መቆጣጠር ተገቢ ስለመሆኑም አሳስበዋል።
ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በቴክኖሎጂ ፣በአሰራር እና በህብረተሰብ ተሳትፎ መከላከል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ የማህበራዊ ሚዲያዎችን አፍራሽ ተልዕኮ ማክሸፍ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በአመራር መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላት መቆጣጠር እንደሚገባም አስረድተዋል።
በተስፋዬ መኮንን
ለተጨማሪ መረጃ
በዌብሳይት https://www.cergcab.et/

