Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ( EHAQ) የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሆስፒታሎች ተሸለመ

CERPHI

በሽልማት መርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መድረኩ እውቅና የምንሰጥበት እና አዲስ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት አዲስ የተገኙ ፈጠራዎች ወደተግባር የሚመጡበት መድረክ መሆኑንም አስረድተዋል።

ባለፉት አመታት በሆስፒታል ሪፎርም የተመዘገቡ ውጤቶችን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል።

ጥራት መዳረሻ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው እና እየተሻሻለ የሚሄድ መሆኑን ያስረዱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ሲሆኑ፤ አዳዲስ አሰራሮች እና ፈጠራዎችን በመጠቀም ሆስፒታሎች አገልግሎቶቻቸውን ማሻሻል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት አረተኛ ዙር ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገበ‍ኡ 30 ሆስፒለታሎች የተሸለሙ ሲሆን ትኩረቱን የጤና ሰራተኛና ባለሙያ የአእናቶችና ህጻናት ጤና፣፣ኮምፕሪሄንስቭ የጤና አገልግሎት ላይ ያደረገዉንና የግሉንም ሆስፒታሎች ያካተተ የአምስተኛዉ ዙር የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት አኢንሼቲቭ የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና ተጠሪ ተቋማትና የሆስፒታል ኃላፊዎች በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *