
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቦራቶሪ Biosafety and Biosecurity program Implementation ተገምግሞ፣ የኮከብ ደረጃ-አራት (Star Level- 4) በማገኘት ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና United Kingdom-Health Security Agency (UK-HSA የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተለት።
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት እና United Kingdom-Health Security Agency (UK-HSA) ጋር በመተባበር፣ በሃገሪቱ የሚገኙ ላቦራቶሪዎች ላይ የባዮሴፍቲ እና ባዮሴኪዩሪቲ ትግበራ ምዘና ያደረገ ሲሆን፣ የማ/ኢ/ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪም ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት፣ የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል። የተገኘው እውቅና በተቋሙ የሚከናወኑ የላብራቶር ምርመራዎች ደህንነት ከባለሞያዎች : ከህብረተሰቡ እና ከተገልጋዩ አንፃር ደረጃው የጠበቀ መሆኑን ያረጋገጠ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ በ Strengthening Laboratory Quality Management System Towards Accreditation (SLMTA) ታቅፎ ያለፉትን ዓመታት ሲተገብር የነበረው የቡኢ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ በመጨረሻው ዙር Assessment ተሰርቶለት Star Level-3 በማግኘት በአገሪቱ የተሻለ አፈጻጸም ካስመዘገቡ ተቋማት አንዱ ሲሆን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይም በውስን የፍተሻ መስክ በISO 15189:2022 መስፈርት እውቅና ለማግኘት (Accredited ለመሆን) ለኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ጥያቄ አቅርቦ ለአሰሰመንት እየተጠባበቀ ይገኛል። ከዚህም ውጪ በዚህ አመት መጨረሻ በክልሉ ያሉ በርካታ የጤና ተቋማትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ይገኛል ።
የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት በክልሉ ላቦራቶሪ እንዲሁም በሆስፒታል ላቦራቶሪ በተገኘው እውቅና ሽልማት፣ ከፍተኛ ደስታ እንደተሳማው እንዲሁም ለዚህ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትን የተቋሙን ሁሉንም ሠራተኞች ከልብ ያመሰግናል !!!!


