Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በክልሉ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ የአሰጣጥ ስርዓትን በማዘመን ህብረተሰቡን ከጤና ስጋት ለመጠበቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ

CERPHI

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ከዞኖች ለተዉጣጡ የጤና ጣቢያ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያዎች በመሰረታዊ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረዉ የሆሳዕና ማዕከል ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በማጠቃለያዉ እንደተናገሩት

ማህበረሰቡን ከየትኛዉም የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ የጤና ስጋት ለመጠበቅ ዉጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል

የክልሉን ማህበረሰቡ የጤናዉ ባለቤት በማድረግ እና በማሳተፍ ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን ቀድመዉ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ ለገሰ ከተከሰተም በኃላ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የተከሰቱ የወርሽኝ ቅኝት ስራዎችን ውጤታማነት ተሞክሮን በማጠናከር ለቀጣይ መዘጋጀት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ለገሰ መረጃን ለዉሳኔ የመጠቀም ባህልን በማዳበር ማህበረሰቡን ከተለያዩ የጤና ስጋቶች ቀድመን መከላከል ይገባል

የታችኛዉን መዋቅር በተለያዩ ጊዝያት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እያበቁ እንደሚገኙ ያወሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ስልጠናዉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ።

ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም የፌም ስራን ይበልጥ ዉጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ጠቅሰው በየተቋማቸዉ የተለየ ወረርሽኝ ከተፈጠረ ለሚመለከተው አካል ፈጥነዉ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ ስልጠናው ቀልጣፋና ውጤታማ ውሳኔዎችን ለመወሰን የሚያግዙ መረጃዎችን ያገኙበት መሆኑን ጠቅሰዉ በክልሉ የሚከሰቱ ማንኛውንም ወረርሽኝን ቀድመዉ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *