Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በክልሉ ከመጋቢት 18 እስከ 21 5ኛው ዙር የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚሰጥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ ።

CERPHI

(ሆሳዕና፦ መጋቢት 15/2018) ከመጋቢት 18 እስከ 21/2018 ዓ.ም ድረስ ቤት ለቤት የሚሰጠውን የ5ኛው ዙር የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻን አስመልክቶ በክልሉ ሕብረተሰብ ተደራሽ ለሆኑ ሚዲያዎች እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለፁት የፖሊዮ በሽታ ህፃናት ለአካል ጉዳት ብሎም ለሞት የሚዳርግ ነው ብለዋል።

የፖሊዮ በሽታ በተፈጥሮ እና በክትባት እጥረት ምክንያት የሚከሰት እንደሆነ በመግለፅ በሽታውን ለመከላከል የተቀናጀ ክትባት በመስጠት መከላከል እንደሚገባም ገልፀዋል።

በ4ኛው ዙር ክትባት ዘመቻ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ህፃናት መከተባቸውን በማስታወስ በ5ኛው ዙር ክትባት ዘመቻ በክልሉ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ህፃናት የተቀናጀ ክትባት እንደሚከተቡ አስታውቀዋል።

በዘመቻውም አምስት ዓመትና ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ከዚህ በፊት ክትባቱን የተከተቡ ይሁን ያልተከተቡ ህፃናት መከተብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በዘመቻው ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኙ የሚዲያ ተቋማት ሚና የጎላ ስለመሆኑ ገልፀው በአመለካከት ቀረፃ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በዘመቻውም የስርዓተ ምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ህፃናት፣መደበኛ ክትባት ያልወሰዱ ህፃናት ፣ በተፈጥሮ እግራቸው ቆልማማ የሆኑ ህፃናት ልየታ እንደሚደረግ ገልፀው ዘመቻውም ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ተደራሽ ሊሆን ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

ዘመቻው የተሳካ እንዲሆን የሚዲያ አላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጉዳዩን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅና ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ ቤተሰብ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በመድረኩም የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ ጨምሮ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች፣ የራዲዮና ቴሌቪዥን ኃላፊዎች፣ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጆችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *