Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በአፍሪካ የጤና ኤክስቴንሽን የሰው ኃይል ፕሮግራሞችን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ከ20 በላይ ከአፍረካ ሃገራት የተውጣጡ የጤናው ዘርፍ አካላት በአዲስ አበባ ከተማ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

CERPHI

የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የጤና ስርዓታችን የጀርባ አጥንት እና በጤና ተቋማት እና በማህበረሰቦች መካከል ያሉ ድልድይ ናቸው” ያሉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፤ በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ለተሻሻለ የጤና ውጤት ብቻ ሳይሆን ለስራ ዕድል፤ ለማብቃት እና ለዕድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።

የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ስርዓቶችን በማጠናከር እና ለህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

የማስተርካርድ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ሰዊት አህደሮም የፋውንዴሽኑን የያንግ አፍሪካ ስራዎች ስትራቴጂ እና በተለይም በአፍሪካ በሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ላይ በማተኮር ለጤና የሰው ኃይል ልማት ያለውን ቁርጠኝነት አጉልተው አሳይተዋል።

በዝቅተኛ ደረጃዎች ያሉ የጋራ የትግበራ ማዕቀፎችን መደገፍ፣ በዘላቂ ፋይናንስ ላይ ስምምነት ማድረግ እና ግልጽ የሆኑ ደረጃዎች እና የአስተዳደር ዝግጅቶች ያሉት የ90 ቀናት የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት ከመድረኩ እንደሚጠበቅ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር መፍትሄ ታደሰ ገልጸዋል።

ጤና ሚኒስቴር እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የአፍሪካን የጤና ኤክስቴንሽን የሰው ኃይል ማጠናከር፡ አሰላለፍ፣ አተገባበር እና ዘላቂነት” በሚል መሪ ቃል ከ20 በላይ የአፍረካ ሃገራት የተውጣጡ የጤና ዘርፍ መሪዎችን፣ አጋሮችን፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን እና የፋይናንስ ድርጅቶችን አሰባስቧል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *